Wednesday, August 31, 2011

አቡነ ጳውሎስ አውሮፕላን ሊገዛላቸው ነው


  • በአባ ጳውሎስ 20ኛ ዓመት በዓለ ሲመት 5 ሚሊዮን ለማትረፍ ታቅዶል፡፡
  • የአዲስ አበባ እና ጠንካራ ሀገረ ስብከቶች ጠቀም ያለ ገንዘብ ይጠበቅባቸዋል ከተሳክ አውሮፕላን ከተገዛ አባ ጳውሎስ በአፍሪካ የመጀመሪያው ይሆናሉ የጳጳሳት ሹመት ኮሚቴ ተቋቁሟል
  • በ18ኛ ሲመት ዓመት ላይ ሰርፕራይዝ ለማድረግ ሀውልት ብለው ጣኦት አቆሙላቸው 
  • በ20ኛው ሲመት ላይ አውሮፕላን ለመግዛት እቅድ ይዘዋል 
  • በ22ኛው ሲመት ላይ ቅዱስ ብለው ፅላት ሊያስቀርፁላቸው ይችላሉ 
  • በ24ኛው ሲመት ላይ……….?????????
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ 5ኛው ፓትርያርክ ሲሆኑ በ2004 ዓ.ም. ዘመነ ፕትርክናቸው 20 ዓመት ይሆነዋል በመሆኑም 20ኛው የበዓለ ሲመት በደመቀ ሁኔታ እንዲከበር እና ከተሰበሰበው ገንዘብ ላይ 5000000 (አምሰት ሚሊዮን) ብር ለነወ/ሮ እጅጋየሁ ለግላቸው ለማትረፍ ገንዘቡን ለመሰብሰብ ምክንያቱ የአውሮፕላን ግዢው እንዲሆን ከየአጥቢያው እና አቅም ካላቸው ሀገረ ስብከቶች ገንዘብ በማሰባሰብ በዓሉን ልዩ ለማድረግ እንቅስቃሴ ተጀምሯል፡፡ በሚሰበሰበውም ገንዘብ ለፓትርያሪኩ ልዩ አውሮፕላን ለመግዛትም ታቅዷል፡፡ 

የጻድቅ ሞት በእግዚአብሔር ዘንድ የከበረ ነው!


By Elizabth Teklehana 

የአባታችን የአቡነ ተክለሃይማኖት አባት ቅዱስ ፀጋዘአብ በሸዋ ቡልጋ ደብረ ጽላልሽ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አገልጋይ ካህን ነበሩ፡፡ መጋቢት 24 ቀን አባታችን ተክለሃይማኖት ተፀነሱ በታህሣስ 24 ቀን በ1190 ዓ.ም አባታችን ጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ከእናታቸው ከቅድስት እግዚሐሪያ እና ከአባታቸው ከቅዱስ ፀጋዘአብ ተወለዱ፡፡ በተወለዱ በ3ኛው ቀን አሐዱ አብ ቅዱስ፣ አሐዱ ወልድ ቅዱስ፣ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ ብለው ፈጣሪያቸውን አመሠገኑ፡፡

የብሎገሮች ቀን



በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያውያ ውስጥ ያለው የብሎገር ብዛት ከጊዜ ወደ ጊዜ በቁጥር እየጨመረ መጥቷል፡፡  በፖለቲካ፣ በማኅበራዊ ኑሮ፣ በእምነት፣ በኪነ ጥበብ ወዘተ ላይ የሚያተኩሩ ብሎጎች ብቅ በማለት ላይ ይገኛሉ፡፡ እኛም ይችን ብሎግ ይዘን የሚቀጥለውን አላማ አድርን ተነስተናል:: 

አንድ አድርገን

አንድ አድርገን
አንዲት  ቅድስት  ቤተ  ክርስቲያንን  በሚመለከት  ዕለት  በዕለት  የሚታየዉ፦ የውስጥና  የውጭ  ችግር ፡ - አደጋና  የወደፊት ስጋት ምን እንደኾነ ኹሉም የእናት ቤተክርስቲያን ልጆች  እንዲያውቁት ፤ የበኩላቸውንም  መፍትሔ  እንዲፈልጉ ፤  ሐሳብ እንዲሰጡ ፤ በክርስትናቸው  የሚጠበቅባቸውን  ሓላፊነት  እንዲወጡ  የክርስቶስን  መስቀል  ለመሸከም  የማይሰቀቅ  ክሣደ  ኅሊና  ኖሯቸው  ለስብከተ  ወንጌልና  ሐዋርያዊ  ተልእኮዋ  መሳካት  ለህልውናዋ  መጠበቅና  ለፍጹም  አንድነቷ  እንዲነሡ  የምታተጋ  ዐውደ  ምጽሓፍ  ወመስተሳትፍ  ናት ። 

Tuesday, August 30, 2011

‹‹ቤተክርስትያኒቷ ትዘጋ›› የሚል ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ

‹‹የገሀነም ደጆች አይችሏትም››


ጊዜው ወርሀ ክረምት ነው :: የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ፆመ ፍልሰታ ወቅት ሲሆን በቤተክርስትያናችን ህግና ስርዓት መሰረት ይህ ጊዜ ዲያቆናት ፤ ካህናት መነኮሳት ፤ ጳጳሳት እና ምእመናን ለሐዋርያት የተገለፅሽላቸው እናታችን ለእኛም በምህረት አትለይን እያሉ በፆም ፤ በፀሎት ፤ በስግደት የሚለምኑበት ጊዜ ነው፡፡

ቦታው በሐረር መንገድ አዋሽ ሰባትን አልፈው ካለው የጉምሩክ የፍተሻ ጣቢያ ትንሽ ኪሎ ሜትር አለፍ ብሎ ከአሰቦት ገዳም መገንጠያ ሳይደርስ ከዋናው አስፋልት አንድ ኪሎ ሜትር ላይ የሚገኝ የአባታችን የአቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ቤተክርስትያን ሲሆን የቦታው ስም ቦርደዴ በመባል ይታወቃል፡፡ ይህ ቤተክርስትያን የሚገኝበት ቦታ ላይ ከ30 የማይበልጡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞች ሲገኙ በቁጥር ከ40 እና ከ50 እጥፍ ልቀው የሚገኙት ግን ሙስሊም ማህበረሰቦች ናቸው፡፡ ይህ ቦታ ለአንድ አፍታም ቢሆን ከነገር እና ከትንኮሳ እፎይ ያለበት ጊዜ የለም፡፡ ቦታ ድረስ ሄጄ በተመለከትኩበት ጊዜ እዚህ ቦታ ላይ ያለው የሙቀት መጠን ክረምት ሳይል በጋ ከ40 ድግሪ በላይ ስለሆነ ቆሞ ማስቀደስ እንደ እግዚሐብሔር መልካም ፍቃድ ፤ ምህረት ፤ ቸርነት እንጂ እንደ እኛ ብርታትና ጥንካሬ እንዳልሆነ ተረድቻለሁ፡፡

Monday, August 29, 2011

‹‹ ፋሽስት ጣልያን አሽቀንጥሮ የጣለልንን ቀንበር መልሰን አንሸከምም ››መምህር ተስፋዬ ሸዋዬ



  • ስልጣነ ክህነት የሚያላብስ ሊቀጳጳስ አሁንም በመንበር ላይ የለም 
  • ፋሽስት ጣልያን አሽቀንጥሮ የጣለልንን ቀንበር መልሰን አንሸከምም 
  • …..በ 1974 ዓ.ም ዶክተሮቹ ጳጳሳት ደካማውን ፓትርያልክ አንከርፍፈው ሮም ወስደው ለፓፓው አሰግደው…….‹‹ ውይ እዚህው ድረስ እንዲያው ደከማችሁ እዛው ካርዲናል ሾሜላችሁ የለም እንዴ እዚያው በማሰልጠን ትምህርት አመሳስሉ›› ተብለው መመሪያ ተቀበሉ 
  • የቤተክርስትያን ሐብቷ ሰው እንጂ ገንዘብ አይደለም 
  • አሁን በቤተክርስትያን ቁንጮ ላይ ሆነው የሚራኮቱት በአሜሪካ በራሽያ በሩማንያ የተማሩ እርስ በርሳቸው የሚናናቁ ናቸው 
  • የተዋህዶ ሐይማኖታችን እምነትና ትምህርት አይለወጥብንም ስርዓታችን አይናወጥብንም መቅደሳችን አይደፈርብንም የሚለው እንቅስቃሴ ለራስ ገፅታ ግንባታ ለማዋል መራወጥ ይታያል፡፡ 
  • ይህ ሁኔታ እንዳይከሰት 1600 ዓ.ም በተጠንቀቅሰ ሲጠብቁ ኖረዋል አሁን ግን የተባለው ሊፈፀም ግድ ስለሆነ የማይቀር ነውና ምዕመኑ ሊሸበር አይገባም 
Click Read More...............

ኡራኤል ቤተክርስትያን አጠገብ ለመናፍቃን 2300 ካሬ ቦታ ሊሰጣቸው ነው


  • ካልጠፋ ቦታ ከዑራኤል ቤተ ክርስቲያን ጋር አጠጋግቶ መስጠቱ ችግር ያስከትላል - የአ.አ. ሀገረ ስብከት
  • ስፍራው ለልማት ከተፈለገ የማልማቱ ቅድሚያ ለእኛ ሊሰጠን ይገባል - ነጋዴዎች
  • የእምነት ተቋማት አድልዎ ሊደረግባቸው አይገባም - የኢትዮጵያ ህይወት ብርሃን ቤ/ክ

ጉዳዩ ውዝግብ አስነስቷል
የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ሊዝ ቦርድ ስፋቱ 2222 ካሬ ሜትር የሆነውን ቦታ፣ በአቶ አርከበ ዕቁባይ የቦርድ ሰብሳቢነት ከሊዝ ነጻ lቤተክርስቲያኒቱ እንዲሰጥ ውሳኔ ተላልፏል፡፡
በዚሁ ውሳኔ መሠረትም ቤተ ክርስቲያኒቱ በስፍራው ለሚገኘው አንድ የኪራይ ቤቶች ቤት 317965.58ሣ. ካሳ በሚያዝያ 4/1998 ዓ.ም. ከፍላለች፡፡ ቦታውን ግን አሁንም አልተረከበችም፡፡ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ መሬት አስተዳደር ባለስልጣን የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ሊዝ ቦርድ የሰጠውን ውሳኔ ተግባራዊ ማድረግ ያልቻለበትን ሁኔታ ሲገል፤ የቦታው አገልግሎት ለቅይጥ አገልግሎት እንጂ ቤተክርስቲያን ያለመሆኑንና ቦታው በዋና መንገድ ላይ የሚገኝና ከፍተኛ የንግድ እንቅስቃሴ የሚከናወንበት ስለሆነ በተፈለገው ፍጥነት ቦታውን ቤተክርስቲያን ማስረከብ እንዳልቻለ በመግለ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለመሬት ልማትና አስተዳደር ባለስልጣን ደብዳቤ ፏል፡፡

Saturday, August 27, 2011

መምህር ግርማ ታገዱ

  • ድቁና እንጂ ቅስና የለኝም በማለታቸው ታግደዋል - ሊቀጳጳስ አባ ቆውስጦስ
  • ማስረጃ በማቅረቤ እግዱ ተነስቶልኛል - መምህር ግርማ
  • በድቁና የሚያገለግል ሰው ይላላካል እንጂ አያጠምቅም
  • እኔ ቅስናዬን ደብቄ ነው

ከስርዓት ውጭ በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች በርካታ ሰዎችን ፀበል አጠምቃለሁ እያሉ ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ ቤት ገዝተዋል የሚል ቅሬታ የቀረበባቸው መምህር ግርማ ወንድሙ፤ የ1.5 ሚ. ብር መኖሪያ ቤትና ፒክአፕ መኪና ያገኘሁት በስጦታ ተገዝቶልኝ ነው ብለዋል - መምህር ግርማ”

Friday, August 26, 2011

ድንግል ማርያም.. ነኝ ባይዋ ሴት ክስ ሊመሰረትባት ነው

ከቀናት በፊት ማርያም ነኝ ብላ የተነሳቸውን ሴት ከ30 ደቂቃ የቪዲዮ ማስረጃ ጋር በብሎጋችን ላይ መዘገባችን ይታወቃል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ይች ሴት በፖሊስ እጅ እንደምትገኝ እና ክስ ሊመሰርትባት እንደሆነ ያለንን መረጃ እንደሚቀጥለው አቅርበነዋል….
  • አንዲት የ19 ዓመት ወጣት ሞታለች
  • እናቴ ከመቃብር በመላዕክት ታጅባ አርጋለች
  • ሦስት ልጆቿን በመንፈስ ቅዱስ ወለድኳቸው ትላለች፤ ባሏም ተስማምቷል
  • ህፃናትን ለሦስት ቀናት፤ አዋቂዎችን ለስምንት ቀናት ስታፆም ነበር
  •  የሥላሴ መንፈስ በእኔ ላይ አድሯል፤ ከእግዚአብሔር የተላክሁ ማርያም ነኝ.. በሚል ድንኳን በመኖሪያ ቤቷ አካባቢ ተክላ ተከታዮች ስታፈራና እምነቷን ስታስፋፋ የነበረችው ሴት በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውላ ምርመራ እየተካሄደባት ነው፡፡


ድንግል ማርያም.. ነኝ ባይዋ ሴት(ትዕግስት ብርሃኑ)
በአምቦ ከተማ ገላን በተባለ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ውስጥ ተወልዳ በ1994 ዓ.ም. ወደ አዲስ አበባ የመጣችው ትዕግስት ብርሃኑ ከ1999 ዓ.ም. ጀምሮ ..ማርያም ነኝ.. በሚል ማሳሳቻ ተከታዮችን አፍርታ እንደ ነበር ከፖሊስ የተገኘ ማስረጃ ይጠቁማል፡፡

Thursday, August 25, 2011

ከእግዚአብሔር በታች ብንፈርድስ?


by Wendemsesha Ayele Kesis 


ነሐሴ ስምንት ተአምረኛ ሆናብኛለች። ወልቂጤ ከተማ ውሎዬን አጠናቅቄ ለጠዋት ሥራ ሰነዶችን በሶፍት ኮፒ ሳዘጋጅ ባደርኩበት ሠፈር ጩኸት ሰማሁ፤ የምሽት ጩኸቶች ምክንያታቸው ስለሚያደናግር ብዙ ጊዜም ስለማያስደስቱ ወጥቶ ማጣራቱን አልፈለግሁም፤ ባለሁበት ሳዳምጥ ቆይቼ ድምጹ ከሠፈሬ ሲርቅ ወደሥራዬ ተመለስኩ። 

‹‹ያለ ነውጥ ለውጥ አይገኝም›› አባ ናትናኤል



      
       ያልተቋጨው የሀዋሳው ጉዳይን በማስመልከት አባ ናትናኤል(የሀዋሳ ደብረ ገነት ቅድስት ስላሴ ቤተክርስትያን አስተዳዳሪ የነበሩ ) እና አባ ጊዮርጊስ (የሞኖፖል ተክለ ኃይማኖት እና የቅዱስ ገብርኤል አስተዳዳሪ የነበሩ) በፊት በተሐድሶ እና ከፕሮቴስታንት አራማጆች(ተስፋ ኪዳነምህረት ማህበር እና ከመሰሎቻቸው )ጋር በመሆን የእግዚሐብሔርን አውደ ምህረት እንዲፈነጩበት ካደረጉ ሰዎች መካከል ሁለቱ ናቸው፡፡በጊዜው ገንዘብ አይናቸውን አሳውሯቸው ፤ ለአውደምህረት የማይመጥኑ ፤ ትምህርቱ የሌላቸው ሰዎችን በመጋበዝ ህዝቡን እዚህ ደረጃ እንዲደርስ ካደረኩ ሰዎች ዋናዎቹ ሲሆኑ አሁንም በሰሩት ስራ ንስሀ እንደመግባት ከእኩይ ስራቸው ሊማሩ ባለመቻላቸው እያስተባበሉ ይገኛሉ፡፡
       ሲኖዶሱ ባቋቋመው አጣሪ ኮሚቴ እንደ ስራቸው ተመዝነው ከተሸሙበት ቦታ ተነስተዋል:: በጊዜው ‹‹ያለ ነውጥ ለውጥ አይገኝም›› ብለው በአውደ ምህረት ላይ የሰበኩ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት የተሰራው ስራ ትክክል አይደለም እኛ ትክክል ነን ፤ ምንም ያጠፋነው ነገር የለም በማለት  ከአንድ መፅሄት ጋር  ያደረጉትን  ቃለ ምልልስ 

Wednesday, August 24, 2011

ጉድ…ጉድ..ጉድ...


በዚህ በስምንተኛው ሺህ አይን የማያየው ጆሮም የማይሰማው ነገር የለም፡፡
‹‹ቅድስት ድንግል ማርያም እኔ ነኝ  እየሱስ ክርስቶስን የምወልደው እኔ ነኝ ፡፡›› ብላ የተነሳች ሴት ተፈጥራለች>>
ድንግል ማርያም እኔ ነኝ



በዚህችው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የዋሓንን አማኝ በማሳት በማታለል የቤተ ክርስቲያንን ዶግማ እና ስርአት ለማጥፋት የሚጥሩ ብዙ ተኩላዎች እንዳሉ የማይካድ እውነታ ነው፡፡ ይህቺ ቤተ ክርስቲያን ከውጪ ያለችበት ከፍተኛ ፈተና ከፊት ተጋርጦ ሳለ እዚሁ በየገዳማቱ በየአድባራቱ ያሉትን የዋሀንን በፈለጉት ሀሳብ በመስበክ ሕዝቡን እያሳቱ እንዳለ ይህ እውነተኛ ምስክር ነው፡፡

Monday, August 22, 2011

እነ በጋሻው ተሀድሶ የተባሉበት 15 ምክንያቶች



‹‹ጊዜው አንድምታ የሚያስፈልገው አይደለም››

ከዚህ በታች ያሉት 15 ነጥቦች ሙሉ የድምፅ እና የምስል መረጃ ካላቸው ትምህርቶች ጥቂቶቹ ሲሆኑ ከእነዚህ የባሳ ለመናገር አንደበትን የሚይዝ ፤ ለመስማት ጆሮን የሚሰቀጥጡ ፤ የቤተ ክርስያናችን አስተምህሮ ያልሆኑ ፤ ከመናፍቃን አካሄድ ባልተለየ መልኩ ስህተት የሆኑ ስብከቶችን የሰበከ ሲሆን ልጁ የተጓዘበትን የምንፍቅና   የክህደት ጎዳና ለማሳያ ያህል ይህን አቅርበንላችዋል፡፡ እነዚህን የመሰሉትን ትምህርቶችን ነው አቶ በጋሻው በቤተ ክርስያናችን አውደ ምህረት ላይ በማን አለብኝነት በግብር ከሚመስላቸው ሰዎች ጋር ሲሰብክ የኖረው፡፡

አቶ በጋሻው ኦርቶዶክስ ነውን?

ቃለ መጠይቅ ከ መምህር ሳህሉ አድማሱ ጋር (በጋሻው ኦርቶዶክስ ነውን? የሚል መፅሀፍ ያሳተሙ )
  • ‹‹ይቅርታ መጠየቅ ማለት ተሸማቆ መኖር ነው ፡፡›› አቶ በጋሻው ደሳለኝ 
  • ‹‹ቤተክርስትያኒቱ በአደባባይ መርቃ ስራ ምደባ ቁልፍ የሰጠቻቸው አገልጋዮች በቤተክርስትያን ላይ ወረራ ሲካሄድ ይህ የቅዱስ ሲኖዶስ ጉዳይ ነው በማለት ችላ ሊሉት አይገባም፡፡›› 
  • ‹‹ዲፕሎማውን ወይም ድግሪውን የሰጠናችሁ ሰንበቴ እንድትጠጡበት አይደለም፡፡›› ተማሪዎች ሲመረቁ ፓትሪያልኩ የሰጡት የሥራ መመሪያ 
  • ‹‹የሀገርን ድንበር የሚጠብቅ ሰራዊት የውጭ ወራሪ ድንገት ቢነሳ የጠቅላይ ጦር አዛዡን ፍቃድ ትዕዛዝ መጠበቅ አይጠበቅበትም›› 
  • ‹‹የአይጥ ምስክር ድንቢጥ እንደሚባለው ጋዜጠኛ ተብዬው ትዝታው ጥያቄውን የሚጠይቀው ደግሞ በጋሻው ነው ፡፡ የጥያቄ እና መልሱ ይዘት እከክልኝ ልከክልህ አይነት ነው፡፡›› 

ሙሉ ቃለመጠይቁን ያንቡት.......

Sunday, August 21, 2011

ጉድ ሳይሰማ......

"ማለዳም። ሰማዩ ደምኖ ቀልቶአልና ዛሬ ይዘንባል ትላላችሁ። የሰማዩን ፊትማ መለየት ታውቃላችሁ፥ የዘመኑንስ ምልክት መለየት አትችሉምን?"- ማቴ 16:3 

  • ከዳንኤል ክብረት ተማሩ …..እምነት እና እውቀት እንዲህ ያደርጋል 
  • ከአቡነ ጳውሎስ ቢሮ የሚወጡ ደብዳቤዎች ጉዳይ 
  • እነ በጋሻው ተሀድሶ የተባሉበት 15 ማስረጃዎች 
  • አቶ በጋሻው ወደ ፍርድ ቤት አመራ 
  • የበጋሻው የቅጥር ደብዳቤ ፎርጅድ ይመስላል 
  • አቶ በጋሻው ኦርቶዶክስ ነውን? 
  • ሁኔታዎች መልካቸውን እየቀየሩ ነው፡፡ 

ሙሉውን ለማንበብ ይጠብቁን.......
‹‹ይጥብቁ አበዛችሁ እኮ ›› የሚል አስተያየት የተሰጠን ሲሆን በአንድ ጊዜ ሁሉን እጄ ላይ ያለውን መረጃ በ1 ቀን ፖስት ማድረግ የምችል ሲሆን ፡፡ ነገር ግን አላማው ሰዎች እንዲያነቡት እና ትምህርት እንዲያገኙበት በተጨማሪም መረጃን ከማካፈል አኳያ ሁሉን ነገር በ1 ቀን ፖስት ማድረግ አስፈላጊ ስላሆነ በሂደት ይጠብቁ የተባሉት ፖስቶች ሁሉን ፖስት የማደርግ መሆኑን በትህትና እገልፃለሁኝ፡፡

እመቤታችን ከማረፏ ከሰዓታት በፊትና በኋላ ምን ሆነ?

ማርያም ስጋኪ ዘተመሰለ ባሕርየ
ተሓፍረ ሞት አኮኑ ሶበ ነጸረ ወርእየ
እንዘ በደመና ብሩህ የዐርግ ሰማየ
እንኳን አደረሰን

እመቤታችን በእናት አባቷ ቤት ሦስት ዓመትአሥራ ሁለት ዓመት በቤተ መቅደስ /ዘጠኝ ወር በቤተ ዮሴፍ/፣ ከመድኃኒታችን ጋር ሰላሣ ሦስት ዓመት ከሦስት ወር ፣ በቤተ ዮሐንስ አሥራ አምስት ዓመት፤ ጠቅላላ ስድሳ አራት ዓመት በዚህ ምድር ኑራለች::

ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ለአገልግሎት ወደ ኤፌሶን በሄደበት ወቅት የቤተ መቅደስ አለቆች ልጆች የነበሩ ደናግል እግሯን እያጠቡ እየተላላኩ ያገለግሏት ነበር:: እመቤታችን ጐልጐታ በሚገኝው የመቃብር ቦታ እየሄደችም አዘውትራ ትጸልይ ነበር:: መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልም በመቃብሩ በምትጸልይበት ጊዜ ከዚህ ዓለም በሥጋ ስለምታርፍበት ሁኔታ ከነገራት በኋላ ታመመች:: ያን ጊዜ አገልጋዮቿና ጎረቤቶቿ ሁሉ በአንድነት ተሰበሰቡ ብዙ ድውያንም ወደእርስዋ እየመጡ ያመሰግኗትና ይፈወሱም ነበር:: እመቤታችንም ደስ ብሏት ትባርካቸዋለች::

Friday, August 19, 2011

መዝሙሮቻችን ድሮና ዘንድሮ

እናስተውል.........
በፊት በፊት የመዝሙር ግጥሞች ሲፃፉ እግዚሐብሔር እንዲመራቸው በፆምና በፀሎት እግዚሐብሔርን መጠየቅ የነበረ ሲሆን አሁን አሁን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ተብሎ የሚወጣው መዝሙር ግጥም ከመናፍቃን የመዝሙር ካሴት ግጥም ኮፒ እየተደረገ መቅረብ ከጀመረ ሰንበትበት ብሏል፡፡ በተጨማሪም ሆን ተብሎ ለቸብቸቦ የሰውን ስሜት እንዲገዛ ተደርጎ ከመፃፉም ባሻገር አንዳች ነገር ለመዝሙር ሰሚው ወንጌልን የማስተላለፍ ሚናው በሙሉ ጠፍቷል ፡፡ ለምሳሌ ለማሳያ ያህለል ዘርፌ ከበደ አወጣሁት ካለችው መዝሙር ሁለት ያህል ግጥሞች አቶ በጋሻው ደሳለኝ ፃፍኩ ያለው ሲሆን በጊዜው እነዚህ ግጥሞች ከመናፍቃኑ ካሴት ምንም ለውጥ ሳይኖራቸው የተገለበጡ በመሆኑ የግጥሙ ባለቤት ግጥሜ ተሰርቆብኛል ሲል አቶ በጋሻው ደሳለኝን ፍርድ ቤት መክሰሱ የሚታወስ ቢሆንም በምን አይነት ሁኔታ የፍርድ ቤቱ ፋይል እንደተዘጋ ግን የታወቀ ነገር የለም፡፡ 

አቶ በጋሻው ደሳለኝ የመናፍቃንን ካሴት እየቃረመ ለእኛ ማቅረቡን የለመደው የቀን ተቀን ስራው መሆኑን ለማወቅ ‹‹የመስቀሉ ስር ቁማርተኞችን›› የሚለውን መፅሀፍ ለመፃፍ የፓስተር መለሰ ወጉን የስብከት ካሴት ቁጥር 107 ገልብጦ የተጠቀመ ሲሆን ይህን ስራውን በዘርፌ ካሴት ላይም ደግሞት ለማየት በቅተናል፡፡ ለማስረጃ ያህል የሚቀጥለውን ካሴት ስቲከር ይመልከቱ 

ቀጣዩን. ...... Click Read More 

Thursday, August 18, 2011

እውን ‹‹ተሐድሶ›› የለምን?

 (በዲያቆን ኅብረት የሺጥላ/ hibretyes@yahoo.com):- ሰሞኑን በተደጋጋሚ ‹‹ተሐድሶ የሚባል ነገር የለም ማኅበረ ቅዱሳን የፈጠረው ወሬ ነው!›› የሚል ንግግር በመስማቴ ይህንን አጭር ማሳሰቢያ ለመጻፍ ተነሳሣው፡፡ በእርግጥ ንግግሩን ቀደም ሲልም ሰምቼው አውቃለሁ፡፡ ነገር ግን መደጋገሙ ሲበዛ በተለይም ግምት የሰጠዋቸው ሰዎች ነገሩን ተቀብለዉት ስመለከት ለካ የሚናቅ ሐሰት የለም አሰኘኝ!

‹ማኅበረ ቅዱሳን የፈጠረው ወሬ ነው!›› ለሚለው ለምን ፈጠረው? ይህን ሐሳብ ፈጥሮ ምን ይጠቀማል? ቢፈጥረውስ እናንተ ተሐድሶ ካልሆናችሁ ምናችሁ ይነካል? የሚል የራሴን ጥያቄ ፈጥሮ ከመጠየቅ በቀር እኔን ስለማይመለከተኝ የማኅበሩ የቤት ሥራ ነውና ራሱ ይጨነቅበት ብዬ አልፌዋለሁ፡፡ ትንሽ ማብራሪያ ለመስጠት የምሞክረው ‹‹ተሐድሶ የሚባል ነገር የለም›› በሚለው አመለካከት ላይ ነው፡፡

 በእርግጥ አንድን ነገር እያለ ‹‹የለም›› ማለት አንድም ሐሰት ዳግመኛም የጥፋት ስልት መሆኑ ይታወቃል፡፡ የአጥፊዎች ሁሉ አውራ የሆነ ሰይጣንም ይህን ስልት በተለያየ መንገድ ሲጠቀምበት ይታያል፡፡

ሰይጣን በሰዎች ልቡና ያድርና ራሱን ደብቆ ክፉ ሥራ ሲያሠራቸው ይኖራል፡፡ በወንጌል እንደተነገረው በጾም፣ በጸሎትና በመንፈሳዊ ሥራ እንዲሁም በተቀደሰ ውሃና አፈር (በጸበል) ኃይሉ ሲደክምበት ‹‹ተቃጠልኩ›› እያለ ይለፈልፋል፡፡ በዚህ ጊዜ ሰይጣን መሆኑ ታውቆ አስፈላጊውን መንፈሳዊ ሥርዓት በማከናወን ያንን ሰው ለቆ እንዲወጣ ይገሠጻል፤ ይረገማል፤ ይገዘታል፡፡ ወዲያውም ለቆ ይሄዳል፡፡
ቀጣዩን....... Click Read More 

“ተሐድሶ የለም” ቀሲስ ተስፋዬ መቆያ



መቀመጫው በሰሜን አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ያደረገው ቀሲስ ተስፋዬ መቆያ በዕለተ ረቡዕ 06/02/2011 በሰርክ ጉባኤ በደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን መድረክ ላይ ተሐድሶ የሚባል ነገር በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የለም በማለት አስተማረ:: እንዲሁም ደግሞ ጸረ ተሐድሶ እንቅስቃሴ እያካሄዱ የሚገኙት ማኅበራት እና ግለሰዎች ላይ ተስፋዬ መቆያ የወቀሳ እና የተቃውሞ ድምጹን አሰምቶዋል:: ቀሲስ ተስፋዬ መቆያ “ተሐድሶ የለም” ብሎ መናገር መብቱ ቢሆንም፤ ነገር ግን የተሐድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴ የሚታገሉ ወገኖችን መወንጀል አይገባውም ነበር::


ቀሲስ ተስፋዬ መቆያ በቤተ ክርስቲያናችን ላይ የተሐድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴ መኖሩን ለምን እንደተቃወመው ለጊዜው የሚታወቅ ነገር የለም:: እንዲሁም ደግሞ በዲያቆን ኅብረት የሺጥላ እውን‹‹ተሐድሶ›› የለምን? በሚል ርዕስ ተሐድሶን በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ጽሑፍ ቀሲስ ተስፋዬ መቆያ ተቃውሞታል:: 

 የተዋሕዶ ልጆች የቤተ ክርስቲያናችን የውስጥ መናፍቃንን ለማጋለጥ በአንድነት በተረባረቡበት በዚህ ወቅት “ተሐድሶ የለም” ብሎ መቃወም የሰባኪው ማንነት ጥያቄ ውስጥ ያስገባዋል:: 

ምሥጢረ ደብረታቦር


አሐደ ለከ ወአሐደ ለሙሴ ወአሐደ ለኤልያስ ንግበር ማኅደረጌታ ሆይ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ፥ በዚህ ሦስት ዳስ ፤ አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱንም ለኤልያስ እንሥራ ›

ቅዱስ ጴጥሮስ

እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፥ እነሆም፥ ከደመናው። በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ። ደቀ መዛሙርቱም ሰምተው በፊታቸው ወደቁ እጅግም ፈርተው ነበር። ኢየሱስም ቀርቦ ዳሰሳቸውና። ተነሡ አትፍሩም አላቸው።ዓይናቸውንም አቅንተው ሲያዩ ከኢየሱስ ብቻ በቀር ማንንም አላዩም። የማቴዎስ ወንጌል 17፡1-8

መምህር ዘመድኩን በቀለ ታስሮ የተፈታበትን ቃለ መጠይቅ

ዘመድኩን ስለበጋሻው ……
  • በጋሻው ተሀድሶም ፕሮቴስታንትም ሙስሊምም የምትለው ሰው ሳይሆን ያልተማረ መሀይምነው: 
  • በጋሻው ህገ ወጥ ሰባኪ ነው፡፡ ከየትኛውም ትምህርት ቤት ሰርተፊኬት ሆነ የሰባኪነት የብቃት ማረጋገጫ ያልተሰጠው ሰው ነው፡፡ ዝም ብሎ አውደምህረት ላይ ነው የቆመው፡፡ ያለመማሩ ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚሐብሔር አይደለም ወደሚል ድፍን ያለ ክህደት ውስጥ ከቶታል ፡፡ 
  • ይህ ልጅ ተመከረም አልተመከረም ዋናው ችግር የእውቀት ችግር ነው ፡፡ የእውቀት ድህነት በምክር የሚመለስ አይደለም 
  • የሚያስተምረው የማያውቀውን እና ያልተማረውን ትምህርት ነው ፡፡ 
  • በድብቅ የተቀረፁትም ነገሮች እየመጡ አቅማቸውን እና አቋማቸው እየታየ ነው:: 
  • የቤተክርስትያኗን አስተምሮ እስከፈጸመ ድረስ ሃዋርያ ነው ፡፡ እስከሳተ ድረስ ደግሞ ይሁዳነው 
  • ፓትርያርኩ ጋር የተጠጋው የተደበቀ መሰሎት ነው፡፡ አርማጌዶን ሲወጣ የተፈጠሩት ሁኔታዎች ልጁን መደበቂያ አሳጡት

ቀጣዩን....... Click Read More 

አለመታደል

ስለ ልጆቿ ችግር የሚያለቅስ አባት ያላት ቤተ ክርስቲያን የታደለች ናት። በፈንታው ደግሞ ስለ እርሷ ማልቀስ ሳይሆን የሚያስለቅሷት፣ ስለ እርሷ የሚያዝኑ ሳይሆን የሚያሳዝኗት፣ ልጆቿን በእንባቸውና በትምህርታቸው አጥር መከታ ሆነው ከመጠበቅ ይልቅ ከቅጽሯ የሚያባርሩ ጨካኞች ያሏት ቤተ ክርስቲያን ደግሞ ሊለቀስላት ይገባል።
ስለ ልጆቻቸውና ስለ ቤተክርስትያን ያለቀሱ አባት
በአክራሪ ሙስሊሞች በተለያዩ የግብጽ አካባቢዎች በክርስቲያኖች ላይ የሚፈጸሙትን ጭፍጨፋዎችና ግድያዎች እንዲሁም ወጣት ክርስቲያን ሴቶችን በግድ እያገቡ ማስለም እና ሌሎች የሰብዓዊ መብት ረገጣዎችን በማሰብ ስለቤተክርስትያ እና ስለልጆቻቸው የሚያለቅሱ አባት


ልጆቻቸውን እና ቤተክርስትያንን  ያስለቀሱ አባት
በአንድ ወቅት አባ ጳውልስ እንዲህ ሲለሉ ተደምጠዋል፡-
ክፍ መሪ ተሰጠን ብላችሁ አታጉረምርሙ።ክፍ መሪ ከሆነም የእናንተ ውጤት ነውThis is what you deserveደግ መሪ ለማግኘት መጀመሪያ ደግ ሆኖ መገኘት ያስፈልጋል‛፡፡ አቡነ ጳውሎስ 

እውነታቸውን ነው እሳቸውን የመሰለ ክፉ መሪ ፤ የልጆቻቸው እምባ የቤተክርስትያናችን በተሀድሶያውያን እና በመናፍቃን መከበብ ምንም ያልመሰላቸው  አባት የተሰጠን ከእኛ ክፋት ቢሆንስ ማን ያውቃል ? ክፉውንም ደጉንም የሚሾም አንድ አምላክ ይወቀው እንጂ፡፡
ከዚያም የሰቆቃው ኤርሚያስ ጸሎት ትዝ አለኝና የመጀመሪያዎቹን አራት ስንኞች እንዲህ እያልኩ አነበነብኩ፤

                        አቤቱ የሆነብንን አስብ፤
                        ተመልከት ስድባችንንም እይ፤                
                        ርስታችን ለእንግድች፤ 
                        ቤቶቻችን ለሌሎች ሆኑ።

ስል ሮሮዬን እግዜር ወዳለበት ወደ ሰማይ አሰማሁ።
                                                               በማይገለጥ የተከደነ የለም በሚባለው መጽሃፍ ውስጥ
                                                               አባ ጳዎለሎስና አባ ገ/መዴህን ሲገመገሙ
                                                               (ከዲዊት አዘነ)
2 ቀን ይጠብቁን..........

Wednesday, August 17, 2011

የዳንኤል ይቅርታ



ከዚህ በፊት የወጣው አይነበብም የሚል አስተያየት ስለተሰጠን አሁን ሊነበብ በሚችል መልኩ ፖስት አድርገነዋል
ቀጣዩን....... Click Read More 

‘’የሀይማኖታችን ጉዳይ የፓትርያርኩ ብቻ አይደለም’’ ሊቀ ትጉሃን ዘሪሁን ሙላቱ


  • ‹የትርፍን ነገር ከነጋዴ አትማከር የሃማኖትንም ነገር ከመናፍቅ አትከራከር› ጠቢቡ ሲራክ
  • ‘’የሀይማኖታችን ጉዳይ የፓትርያርኩ ብቻ አይደለም የኦርቶዶክሳውያን ሁሉ ጉዳይ ነው’’
  • ድንግል ማርያም ሥላሴን ወልዳለችን ብሎ መጠየቅ የቤተክርስትያን አስተምሮ አይደለም
  • ሥላሴን ወልዳለችን? ብሎ መጠየቅም ሆነ መመለስ ያስወግዛል ምክንያቱም ቤክርስትያናችንን ሦስት አማልክት እንደምታመልክ የሚያስመስል ፤ ሥላሴን ወልዳለችን? ብሎ በመጠየቅ ምዕመናን ‹‹አዎ ›› ካሉ አብ ፤ ወልድ ፤ መንፈስ ቅዱስ ሥጋ ለበሱ ይላሉ ብሎ በመተቸት በዚህ ስልታዊ ማፈግፈግ እናደርጋለን በማለት ‹‹አዎ ›› ካላሉ ሥላሴ አትበሉ የሚለውን ትምህርታችንን እንቀጥላለን ብለው የተጠቀሙበት የማምታቻ ዘዴ ነው ::
  • የመጀመሪያው ተሐድሶ ኤራሞስ የተባለው ሰው ከአምስት ያላነሱ ሥላሴ የሚሉ ቃላትን ከመፅሐፍ ቅዱስ አስወግዷል ፡፡ ምክንያቱም ሥላሴ የሚለውን መረዳት ስላቃተው ነው፡፡ 
  • ሁለተኛ ሰባኪ ሥላሴ አትበሉ የሚለው ሶስት አማልክት መስለው ስለታዩት ነው ፡፡ በዚህም ብዥታ ምክንያት እንደ ማስረጃ ድንግል ማርያም ሥላሰሴን ወልዳለች ማለት ክህደት ነው፡፡ይህ አመለካከቱ እንኳን በመፅሀፍ ቅዱስ በቅዱስ ቁርአን የተወገዘ ነው(ሱራ 4፡171)
“የሃይማኖታችን ጉዳይ የፓትርያርኩ ብቻ አይደለም” የሚለው ሊቀ ትጉሃን ዘሪሁን ሙላቱ ከቅ/ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የመጀመሪያ ዲግሪውን በሥነ መለኮት፣ ሁለተኛ ዲግሪውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በድኅረ ምረቃ መርሐ ግብር በፊሎሎጂ ትምህርት ተመርቋል። በአሁኑ ወቅትም ደግሞ የዶክትሬት (ፒ.ኤች.ዲ) ጥናቱን በማገባደድ ላይ ነው። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ ተሐድሶ እንቅስቃሴ ወቅታዊ ሁኔታ እና ቤተ ክርስቲያኒቱ በምትከተለው አስተምህሮ ዙሪያ ከዕንቁ መጽሔት ጋር ያደረገው ቃለ ምልልስ እንደሚከተለው ቀርቧል

ቀጣዩን Click Read More


Tuesday, August 16, 2011

ሞት ዘረፈን

እንግዲህ መቃብር ጠንክረህ ተማር
ድጓ ተሸክሞ መጣልህ መምህር

1. ብፁዕ አቡነ ይሥሓቅ (1927 - 2003 .)
  • ‹‹የምናሠለጥናቸው በሌላ ቋንቋ ተናግረው የሌለ ሃይማኖት እንዲያመጡ አይደለም፡፡›› (ብፁዕ አቡነ ይሥሓቅ በ1991 ዓ.ም ከተናገሩት)
  • ብፁዕነታቸው በድንገተኛ ሕመም ማረፋቸው የተሰማው ሐሙስ የካቲት 24 ቀን 2003 ዓ.ም ዘጠኝ ሰዓት ገደማ በመንበረ ፓትርያርኩ ከሚገኘው ማረፊያ ቤታቸው ነው፡፡
  • በቤተ ክርስቲያን የዕለቱን ሥርዓተ ቅዳሴ ተካፍለው በደህና የተመለሱት ብፁዕነታቸው በድንገት ማረፋቸው የታወቀ ሲሆን መንስዔው ከልብ ጋር የተገናኘ ሳይሆን እንደማይቀር ተብሎ በባዶ መላምት አልፏል፡፡
  •  ‹‹ብፁዕነታቸው በመንፈሳዊው ትምህርት የተሟላ ሊቅነት ያላቸው፣ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን በኩል እግዚአብሔርን በዝማሬ መላእክት፣ ሕዝበ ምእመናንን በትምህርት፣ በስብከተ ወንጌል እና በጸሎተ ቡራኬያቸው ያገለገሉ ያሬዳዊ ቅርስነበሩ፡፡›› (ዜና ሕይወታቸው)
2. ብፁዕ አቡነ በርናባስ

  •  "የትምህርት መጨረሻው መልካም ሥራ ነው፡፡" (ብፁዕ አቡነ በርናባስ) 
  • ‹‹የሲኖዶሱ አካሄድ ውኃ ወቀጣ ሆኗል፤ ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር፣ ከግለሰብ ይልቅ ለቤተ ክርስቲያን መወገን አይሻልም ወይ?››(ብፁዕ አቡነ በርናባስ) 
  • ግንቦት 21 ቀን 2003 ዓ.ም ከሌሊቱ 10፡00 ግድም በድንገተኛ ሕመም በተወለዱ በ92 ዓመታቸው ያረፉት የምዕራብ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ በርናባስ 
  • ግንቦት 16 ቀን ከተፈጸመው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ መጠናቀቅ በኋላ ግንቦት 19 ቀን በሀገረ ስብከታቸው መኪና ወደ ባሕር ዳር ያመሩት ብፁዕነታቸው ደብረ ማርቆስ ከተማ ሲደርሱ ድካም እንደሚሰማቸው በመግለጽ በምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት መንበረ ጵጵስና አድረው በበነጋው ጉዟቸውን ቀጥለው እንደ ነበር ተገልጧል፡፡ የዕድሜ ባለጸጋ የሆኑት ብፁዕነታቸው በባሕር ዳር መንበረ ጵጵስናቸው ቅዳሜ ግንቦት 20፣ ከቀኑ 8፡00 ላይ ከደረሱ በኋላ ከምሽቱ 3፡00 ላይ ነበር ያረፉት

አምላክ : ይማርዎ



አምላክ : ይማርዎ

በንስሐ ፡ አክማ
በትምህርት ፡ ሠይማ
በቅዱሳን ፡ ማማ
በመንበሯ ፡ ሾማ
በክብር ፡ ሸልማ 

«ወዮልኝ፣»


«ወዮልኝ፣»

           
         ድካማቸውን አይተው፥ ጉድለታቸውን አስተውለው፥ ራሳቸውን የሚገሥጹ፥ በራሳቸው የሚፈርዱ ሰዎች ብፁዓን (ንዑዳን፥ ክቡራን) ናቸው። ያለፈውን ዞር ብሎ በማየት፥ የቆሙበትን በማስተዋል፥ ወደፊት ሊመጣ የሚችለውንም አሻግሮ በ መመልከት፦ «ወዮልኝ፤» ብሎ ራስን ማስጠንቀቅ መንፈሳዊነት ነው። በተሰጣቸው ጸጋ ሳይኰፈሱ ፥ በአገልገሎት ብዛት ሳይጋረዱ፥ ወደ ውስጥ ማየት የአእምሮ መከ ፈት ነው። «አይገባኝም ፥ ሳይገባኝ ነው፤» ማለት የእግዚአብሔርን ቸርነት መግለጥ፥ ለጋስነቱን መመስከር ነው። በምድርም በሰማይም (በሰውና በእግዚአብሔር ዘንድ) ትሑት ሰብእና፥ ቅን ልቡና ይዞ መገኘት ነው። «ወዮልኝ፤» ያለ ታላቁ ነቢይ ኢሳይያስ ነው። እርሱም ከዓበይት ነቢያት አንዱ ነው።

መምህር ዘመድኩን በቀለና እና ዲ/ን ደስታ ጌታሁን በፖሊስ ተይዘው ታሰሩ

            


ሰበር ዜና ፡ መምህር ዘመድኩን በቀለና እና ዲ/ን ደስታ ጌታሁን በፖሊስ ተይዘው ታሰሩ፡፡ ከክፍለ ከተማቸው ውጭተይዘው መወሰዳቸው ሁሉንም አስገርሟል፡፡ ዛሬ ነሐሴ 9 ቀን 2003 ዓም በጠቅላይ ቤተ ክህነት የገዳማት አስተዳደር ዋና ጸሐፊ ዲ.ን ደስታ እና መምህር ዘመድኩን በቀለ በመጋቤ ሐዲስ? በጋሻው ደሳለኝ ከሳሽነት ቦሌ... ክፍለ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው በዋስ መፈታታቸው ተሰማ፡፡ 

Monday, August 15, 2011

የላይ ቤት ጥሪ ወይስ ሌላ ሤራ?

"በእንተ ቢጽ ሐሳውን ወበእንተ ዜና ዕረፍቶሙ ለአበዊነ":- የአባቶቻችን በ2 ዓመታት ውስጥ ተደጋጋሚና ድንገተኛ ዕረፍት የላይ ቤት ጥሪ ብቻ ወይስ ሌላ ሤራ ያለበት?

  • አቡነ አረጋዊ የቅድስት ሥላሴ ካቴዴራል የበላይ ጠባቂ ሊቀ ጳጳስ በጠና ታመዋል፡፡



ለአብነት ተማሪዎች አዳሪ ትምህርት ቤት ሊሠራላቸው ነው

ሞአ አንበሳ የዘውድ ምክር ቤት በላሊበላና አካባቢዋ ለሚገኙት ወደ ሦስት ሺሕ ለሚጠጉ የአብነት (ቆሎ) ተማሪዎች አገልግሎት የሚውል አዳሪ ትምህርት ቤት በአምስት ሚሊዮን ብር ለማሠራት የሚያስችል ፕሮጀክት ቀርፆ ለተግባራዊነት አስፈላጊውን እንቀስቃሴ በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ እስካሁንም ባካሔደው እንቅስቃሴ ሥራውን የሚከታተልና የሚያስተባብር ኮሚቴ ያዋቀረና ለሕንጻው ግንባታ የሚውል ቦታ ማግኘቱን አስታውቋል፡፡

ፅንሰታ ለማርያም


እንኳን ለፅንሰታ ለማርያም በዓል ነሐሴ 7 በሰላም አደረሳችሁ


ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተፀነስኪ
አላ በሩካቤ ዘበሕግ እምሐና ወኢያቄም ተወለድኪ

ድንግል ሆይ በኃጢአት ፍትወት የተፀነስሽ አይደለም ፤
በሕግ በሆነ ሩካቤ ከሐና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ
አባ ሕርያቆስ በቅዳሴ ማርያም
ጴጥርቃ እና ቴክታ የሚባሉ ሰዎች በኢየሩሳሌም በአንድነት ተጋብተው ይኖሩ ነበር: እነዚህም በእግዚአብሄር የሚያምኑ የተወደዱጻድቃን ደግ ሰዎች ነበሩ:፡ እነዚህም ሰዎች በእግዚአብሄርም በሰውም ዘንድ የተመሰከረለላቸውባለጸጎች ነበሩ::ነገር ግን የሚወርሳቸው ልጅአልነበራቸውምና መካን ነበሩ:፡

ብፁዕ አቡነ ሚካኤል አረፉ




ብፁዕ አቡነ ሚካኤል
የሰሜን ምዕራብ ትግራይ የሽሬ እንዳሥላሴ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሚካኤል ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። እግዚአብሔር አምላክ ነፍሳቸውን በአብርሃም እቅፍ ያሳርፍልን። ለወዳጅ ዘመድ በሙሉ መጽናናትን ያድልልን።
(ዝርዝሩን ወደፊት እናቀርባለን።)

Sunday, August 14, 2011

በቅዱሳን ደም መጠየቅ እንዴት ያስፈራል?


በእግዚአብሔር አርአያና አምሳል የተፈጠረን የሰው ልጅ ነፍስ ማጥፋት ታላቅ ክፋት፣ ታላቅ በደል ነው፡፡ ይህንንም ጌታችን ‹‹እናንተ ግብዞች ጸፎችና ፈሪሳውያን የነቢያትን መቃብር ስለምትሠሩ፣ የጻድቃንንም መቃብር ስለምታስጌጡና ‹በአባቶቻችን ዘመን ኖረን በሆነስ በነቢያት ደም ባልተባበርናቸውም ነበር ስለምትሉ ወዮላችሁ፡፡ እንግዲያስ የነቢያት ገዳዮች ልጆች እንደሆናችሁ በራሳችሁ ላይ ትመሰክራላችሁ፡፡ እናንተ ደግሞ የአባቶቻችሁን መስፈሪያ ሙሉ ፤እናንተ እባቦች የእፉኝት ልጆች፣ ከገሃነም ፍርድ እንዴት ታመልጣላችሁ? ስለዚህ እነሆ ነቢያትንና ጥበበኞችን ፃፎችንም ወደ እናንተ እልካለሁ፤ ከእነርሱም ትገድላላችሁ፤ ትሰቅሉማላችሁ፤ ከእነርሱም በምኩራባችሁ ትገርፋላችሁ፤ ከከተማም ወደ ከተማ ታሳድዳላችሁ፤ ከጻድቁ ከአቤል ደም ጀምሮ በቤተ መቅደስና በመሰዊያው መካከል እስከ ገደላችሁት እስከ በራክዩ ልጅ እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ በምድር ላይ የፈሰሰው የጻድቅ ደም ሁሉ ይደርስባችሁ ዘንድ፡፡›› በማለቱ እንረዳለን፡፡ (ማቴ 23፥29-36)

በቅዱሳን ደም መጠየቅ እንዴት ያስፈራል? ጌታችን ‹‹ወዮላችሁ››፣‹‹እናንተ እባቦች፣ የእፋኝት ልጆች››፣ ‹‹ከገሃነም ፍርድ እንዴት ታመልጣላችሁ?›› ‹‹በምድር ላይ የፈሰሰው የጻድቅ ደም ሁሉ ይደርስባችሁ ዘንድ›› በማለቱ የበደሉን ታላቅነት ፤ የቅጣቱንም አስከፊነት አመልክቷል፡፡ ወንድሙን ከገደለው ቃየል ሳይማር በነፍሰ ገዳይነት የተገኘው ላሜሕ ‹‹እኔ ጎልማሳውን ለቁስሌ ብላቴናውንም ለመወጋቴ ገድዬዋለሁና ቃየልን ሰባት እጥፍ ይበቀሉታል፤ ላሜሕን ግን ሰባ ሰባት እጥፍ›› ብሏል፡፡ (ዘፍ 4፥24)

‹እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ››

ስለሚያስቷችሁ ሰዎች ይህንን ጽፌላችኋለሁ 1ኛ ዮሐ.2፥27

ሐሰት አንናገርም፤ እውነትንም አንደብቅም

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ የተነጣጠረው የ”ተሐድሶ” ዘመቻ ውጥን ብዙ ዐሥርት ዓመታት ያለፉት ቢሆንም ከ1992 ዓ.ም. የካቲቲ ወር ጀምሮ ግን ማኅበረ ቅዱሳን ተጨባጭ በሆኑ የምስልና የድምፅ ማስረጃዎች ዘመቻውን በማጋለጥ የቤተ ክርስቲያናችን ቅዱስ ሲኖዶስ ውግዘት ማስተላለፉ ይታወቃል፡፡ ከዚያ በኋላ “ተሐድሶ” ስልቶቹን በመቀያየር ሃይማኖታችንን ለማጥፋትና በሌላ ፕሮቴስታንታዊ አስተምህሮ ለመተካት የሚያደርገውን ሩጫ ቀጥሏል፡፡ በመሆኑም ማኅበረ ቅዱሳን ካለፈው ነሐሴ 2002 ዓ.ም ጀምሮ ይፋዊ የሆነ ከእነዚህ ሴረኞች ቤተ ክርስቲያንን የመጠበቅ እንቅቃሴ ጀምሯል፡፡ የሐመር መጽሔት ልዩ እትምን በማዘጋጀት የተጀመረውን አገልግሎት በሌሎችም በኅትመትና ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያዎች ከካህናቱ ከሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶችና ከሕዝበ ክርስቲያኑ ጋር ፊት ለፊት በተደረጉ ውይይቶች በመታገዝ ሰፊ ግንዛቤ መፍጠር ተችሏል፡፡ በዚህም የ”ተሐድሶ”ን ምንነት፣ መሠረት፣ ግብና ዓላማ፣ ስልት፣ ያለበትን ደረጃ፣ በሌሎች እኅት አብያተ ክርስቲያናት ፈጥሮት የነበረውን ቀውስና መዘዝ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ዒላማ ለማድረግ በይፋ በተለያዩ የኅትመት ውጤቶች እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ ለማብራራት ጥረት ተደርጓል፡፡

ፈቃደ እግዚአብሔርን እንዴት ማወቅ ይቻላል?


ፈቃደ እግዚአብሔርን እንዴት ማወቅ ይቻላል?» የሚለው የሰው ሁሉ ጥያቄ ነው። ብዙዎቻችን መመዘኛችን ሥጋ ዊ በመሆኑ ፈቃደ እግዚአብሔርን ለማወቅ፥ ለመቀበልም እንቸገራለን። የሚነገረው ሁሉ ለኅሊናችን መልስ ስለማይሆን አጥ ጋቢ መልስ አላገኘሁም እንላለን። ለምሳሌ፦ ከአይሁድ የተላኩ ካህናትና ሌዋውያን፦ መጥምቀ መለኰት ቅዱስ ዮሐንስን፦ «እንኪያስ አንተ ማነህ? አንተ ኤልያስ ነህን?» ባሉት ጊዜ፦ «አይደለሁም ፤» ብሏቸዋል። ዮሐ ፩፥፳፩። ነቢዩ ኤልያስ በእሳት ሠረገላ ወደ ሰማይ ቢያርግም በስሙ የተነገረ « እነሆ፥ ታላቋና የምታስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ሳትመጣ ቴስብያዊው ኤል ያስን እልክላችኋለሁ።» የሚል ትንቢት አለ። ሚል ፬፥፭። ይኽንን ይዘው ነው፥ «ኤልያስ ነህን ?» ያሉት። ዮሐንስ «አዎን ነኝ፤» ማለት ይችል ነበር። ምክንያቱም ጌታችን ፦ «ልትቀበሉትስ ብትወዱ ፥ ይመጣ ዘንድ ያለው ኤልያስ ይህ ነው።» በማ ለት እንደመሰከረለት በሁሉ ኤልያስን ይመስለዋልና። ማቴ ፲፩፥፲፬። ነቢዩ ኤልያስ፦ ፀጉራም ፥ጸዋሚ ፥ተሐራሚ፥ ዝጉሐዊ፥ ባሕታዊ ፥ ድንግላዊ ነው። ቅዱስ ዮሐንስም ልብሱ የግመል ፀጉር ሆኖ፦ ጸዋሚ ፥ ተሐራሚ ፥ ዝጉሐዊ ፥ባሕታዊ ፥ ድንግ ላዊ ነው። ይሁን እንጂ «አይደለሁም፤» ያለው፦ «ነኝ፤» የሚለው እውነት ለአይሁድ ለኅሊናቸው መልስ ስለማይሆን ነው። ለእኛም ስለ ፈቃደ እግዚአብሔር የሚነገረው እውነት ሁሉ ለኅሊናችን መልስ አይደለም። 

ገንዘቤን ሳትሰጠኝ ትሄዳለህን?


ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ዘቁስጥንጥንያ፣ ኤጲፋንዮስ ዘቆጵሮስ እና ቅዱስ ዮሐንስ ዘኢየሩሳሌም እኒህ ሦስቱ በአንድነት ሲማሩ አድገዋል:: ዮሐንስ ዘኢየሩሳሌም ኤጲስ ቆጶስነትን በተሾመ ጊዜ ሰይጣን ልቡን በፍቅረ ንዋይ አታለለው /ተዋጋው/ ከዚህም የተነሣ በሚገኝበት አዳራሽ የወርቅ ሰሃን የብር ፃህል ጽዋ አሠርቶ ነበር:: ኤጲፋንዮስ ይህን እየሰማ ሲአዝን:: ከእለታት አንድ ቀን ቦታይቱን እጅ የሚነሣ መስሎ ሊመክረው ቢመጣ በዚሁ አዳራሽ ተገኝለት:: ወንድሜ የቆጵሮስ ሊቃውንት ደጋግ እንደሆኑ ታውቃለህ:: በዚህ አዳራሽ ልገኝላቸው ስጠኝ አለው:: ሰጠው:: እየሰበረ ለነዳያን ይመጸውተው ጀመረ:: ገንዘቤን ስደድልኝ ሲለው ቆየኝ እያለ ሰነበተ:: በሚሄድበት ጊዜ ሄድሁልህ አለው:: ገንዘቤን ሳትሰጠኝ ትሄዳለህን? ብሎ ልብሱን ያዘው:: ዘወር ብሎ እፍ ቢለው ሁለት ዓይኑን ነሣው /አጠፋው/:: ከጫማው ወድቆ ያለቅስ ጀመር:: አንዱን ለዝክረ ነገር ትቶ አንድ ዓይኑን አብርቶለታል:: እርሱም ይህ ምክር ተግሣጽ ሆኖት እስከ ዕለተ ሞቱ ሲመጸውት ኑሯል:: ሲሞት አንድ አላድ እንኳን አልተገኝበትም:: በረከቱ ትድረሰንና ብጹ አብ ቅዱስ ዮሐንስ ዘኢየሩሳሌም “ኑባሬ ሃይማኖት” በተሰኘው የነገረ ሃይማኖት መጸሐፉ የታወቀ ሊቅ ነው:: /ከዚህ ምን እንማራለን?/

ምንጭ :‐ የሃይማኖተ አበው ትርጓሜ የብራና ቅጅ ያልታተመ

Friday, August 12, 2011

ቅዳሴ ማርያም...ንባቡ እና ትርጓሜው

አባ ሕርያቆስ የደረሰው 
ከቀድሞ አባቶች ጀምሮ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣው ንባቡ እና ትርጓሜው 
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ሊቃውንት እንደ ፃፉትና እንደ ተረጎሙት

በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት የሚያምኑ እና የሚማፀኑ ሁሉ ውዳሴዋን እና ቅዳሴዋን በመማርና በማስተማር በመፀለይም ጭምር እንዲጠቀሙበት መፅናናትም እንዲያገኙበት ከአበው ሲወርድ ሲዋረድ የቆየውን ንባቡን ከነትርጓሜው በዚህ መልክ አቅርበንላችዋል፡፡

ይህን የእመቤታችንን ቅዳሴ ማርያም በዚህ በፍልሰታ በፆም ወራት ቤተክርስትያን ተገኝተው ለመስማትም ሆነ ለማንበብም ለማይችሉ በተለያየ ሀገራት ለሚገኙ ወገኖች በቀላሉ እንዲያነቡ ተደርጎ የተዘጋጀ

THE VIRGIN'S FAST



The Pope Shenouda III series on the topic of “The holy virgin saint Mary” 

Deacon Hibret Yeshitila

The Church celebrates the fast of our Lady the Virgin beginning with the first of Mesra, (the 7th of August). It is a fast for which people care very much, and they practice it with forceful ascetism. Some add days to it, in regard of the great love of people for The Virgin.

The fast of The Virgin is an occasion for spiritual renaissance in the majority of churches.

They prepare a spiritual program for daily sermons, and daily masses too in some churches, even the churches which are not named by the name of The Virgin. There is a great feast for our Lady The Virgin, which is celebrate  in her ancient church in Mostorod.

'' ጻድቅ ሆኖ ወደ ቤቱ ተመለሰ” ሉቃስ 18:14


 ዲያቆን ሳሙኤል ብርሃኑ

ከላይ ያለውን ቃል የተናገራው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን ቃሉንም የተናገረው እራሳቸውን ስለሚያመጻድቁና ሌላውንም ስለሚንቁ ሰዎች በምሳሌ ሲያስተምር ነው። ሁለት የተለያየ ህብረተሰብን የሚወክሉ ሰዎች ለጸሎት ወደ ቤተ መቅደስ እንደሔዱ እና ሁለቱም ስመ እግዚአብሔርን ጠርተው ጸሎት ቢያቀርቡም አንደኛው ብቻ ጸድቆ ወደቤቱ እንደ ተመለሰ ይናገራል።ለጸሎት እንደ ሄዱ ከተነገረላቸው መካከል አንዱ ፈሪሳዊ ነው።

‹‹የኢትዮጵያ ድኳኖች ሲጨነቁ ዐየሁ›› ዕንባ 3.7




ኢትዮጵያ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የአሥራት አገር ናት፡፡ ሊቃውንትም ነቢያት የተነበዩትን ትንቢት የቆጠሩትን ሱባዔ መሠረት በማድረግ ቅድስት ድንግል ማርያም በኪደተ እግሯ ኢትዮጵያን መባረኳን ያስተምራሉ፡፡ ነቢዩ ዕንባቆም «የኢትዮጵያ ድኳኖች ሲጨነቁ ዐየሁ፤» ዕንባ. 3፡7 ብሎ የተናገረው ቃለ ትንቢት እመቤታችን የኢትዮጵያን አውራጃዎች ለመባረኳ ማስረጃ መሆኑን ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ይተረጉማሉ፤ ያመሠጥራሉ፡፡

አኰቴት ዘተዋሕዶ አዲስ የቴሌቪዥን መርሐ ግብር

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያንን እምነት ፤ ስርዓት ፤ ትውፊት እና ታሪክ የሚያስተምር አዲስ የቴሌቪዥን መርሐ ግብር 
እሁድ ከቀኑ 6፡30 – 7፡30
EBS ቴሌቪዥን በመላው ዓለም  ይሰራጫል፡፡


‹እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ››

Thursday, August 11, 2011

አሰግድ ሳህሉ ማነው ?



  • ‹‹ኢየሱስ ክርስቶስ አሁንም በአብ ቀኝ ቆሞ ያማልዳል፤›› አሰግድ ሣህሉ
  • ‹‹የክርስቶስ ሥጋ እና ደም ተቀበልንም አልተቀበልንም ለውጥ የለውም›› አሰግድ ሣህሉ
  • ‹‹የእውነት ቃል አገልግሎት›› የተባለ የተሐድሶ ኑፋቄ አራማጅ ድርጅት የመሠረተ ነው
  • ‹‹ሙሉ ወንጌል›› አማኞች የጸሎት ቤት በተካሄደው ጉባኤ ላይ ከመሰሎቹ ጋራ ተካፍሎ ሲወጣ ተደርሶበታል
የፕሮቴስታንታዊ-ተሐድሶ-ኑፋቄ አራማጅ - አሰግድ ሣህሉ እንደ ማሳያ
አሰግድ ሣህሉ በደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤተ ክርስቲያን የዉሉደ ያሬድ ሰንበት ት/ቤት የተሐድሶ ኑፋቄን ለማስፋፋት፣ አንዳንድ የሰንበት ት/ቤቱን ወጣቶች ከእናት ቤተ ክርስቲያን ወደ ‹‹ሙሉ ወንጌል›› አዳራሽ ለመውሰድ ሲያደርግ የቆየውን እንቅስቃሴ አስመልክቶ በጥብቅ ሲከታተል በቆየው የሰንበት ት/ቤቱ ሥራ አመራር ኮሚቴ የተዘጋጀው ባለ 40 ገጽ ሰነድ ያስረዳል፡፡ እንደ ዘገባው ማብራሪያ አሰግድ ሣህሉ ከሚኖርበት ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 11/12 የቤት ቁጥር 417 በተለምዶ ቡልጋሪያተብሎ ከሚጠራው የደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል - የከርቸሌው ሚካኤል አካባቢ ያለሰበካው ወደ ደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤተ ክርስቲያን መጥቶ በዉሉደ ያሬድ ሰንበት ት/ቤት በ1985 ዓ.ም የተመዘገበው ሰንበት ት/ቤቱ በወቅቱ ያጋጠመውን የአገልግሎት መዳከም ተመልክቶ ስውር የተሐድሶ ኑፋቄ ተልእኮውን ለማራመድ እንዲያመቸው ነው፡፡

ትንቢቱ ሲፈጸም

ትንቢቱ ሲፈጸም በመጽሐፍ ያለው፣
ወገኔ አትደንግጡ ይህ ሊሆን ግድ ነው።
ቅዱሳን ሳይቀሩ የተመረጡቱ፣
በመጨረሻው ቀን በዓለም እንዲስቱ፣
ቀድሞ በመጽሐፍ ተነግሯል ትንቢቱ።

ውዳሴሃ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ ዘይትነበብ በዕለተ ሐሙስ

በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት የሚያምኑ እና የሚማፀኑ ሁሉ ውዳሴዋን እና ቅዳሴዋን በመማርና በማስተማር በመፀለይም ጭምር እንዲጠቀሙበት መፅናናትም እንዲያገኙበት ከአበው ሲወርድ ሲዋረድ የቆየውን ንባቡን ከነትርጓሜው በዚህ መልክ አቅርበንላችዋል፡፡

ይህን የእመቤታችንን ውዳሴ ማርያም በዚህ በፍልሰታ በፆም ወራት ቤተክርስትያን ተገኝተው ለመስማትም ሆነ ለማንበብም ለማይችሉ በተለያየ ሀገራት ለሚገኙ ወገኖች በቀላሉ እንዲያነቡ ተደርጎ የተዘጋጀ

Wednesday, August 10, 2011

ተሐድሶ ማለት እኔ ነኝ…..አሰግድ ሳህሉ

አሰግድ ሳህሉ ነሐሴ  2003 ዓ.ም ከማራኪ መፅሄት ጋር ያደረገው ኢንተርቪው

አሰግድ ፡- ተሐድሶ ማለት ምን ማለት ነው አለችኝ ? አንዷ አገልግለን ስንወጣ ባለፈው ናዝሬት ላይ  እኔም አሰግድ ማለት ነው አልኳት፡፡ ተሀድሶ የሚባል ድርጅት ለመኖሩ እርግጠኛ አይደለሁም መኖሩን ሳውቅ ያኔ ሌላ መልስ ይኖረኛል ፡፡ ይህን ስም የተሸከምኩት 18 ዓመት ነው ፡፡

ሙሉ ዘገባውን ይመልከቱ ........

Tuesday, August 9, 2011