Monday, September 24, 2012

አያት ኦርቶዶክስ ፤ አባት ካቶሊክ ፤ ልጅ ‘ONLY JESUS’


  •  ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ፤ ካቶሊክና ONLY JESUS … በሶስት ትውልድ ሶስት ሃይማኖት!!!!
  •   ምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴር አቶ ደመቀ መኮንን ለክረምት ወደ ቤተሰብ ሲሄዱ እንደ ልጅነታቸው  ቁርዓን በመቅራት እና የአባታቸውን ማሳ በማረስ  ጤፍ ፤ በቆሎና ዳጉሳ በመዝራት አባታቸውን በስራ ያግዙ ነበር፡፡
  •   አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝን ስንተኛ ካዎ እንበላቸው?
  •  Washington DC & # 2176 “SON OF WOLAITA’S KING”
(አንድ አድርገን መስከረም 14 2005 ዓ.ም)፡- ዘወትር ሰዎች ስልጣን ላይ ስላለ ሰው እጅጉን የማወቅ ጉጉት ያድርባቸዋል ፤ አይደለም ጠቅላይ ሚኒስርን የመሰለ ዙፋን ይቅርና ሌላም ስልጣን ቢሆን ብዙ ይባላል ብዙም ይወራል ፤ ስልጣን ላይ የነበረው ሰው ከስልጣን ሲወርድም ምን አይነት ስራ ሲሰራ እንደነበር የማወቅ ጉግታቸው ይጨምራል ፤ እዚህ ግቡ የማይባሉ ሰዎች ወንበሩን ሲይዙት የሁሉም ሰው አይን ውስጥ ይወድቃሉ ፤ ከዚህ  በፊት “ቀይ መብራት” ብለን ባቀረብነው ጽሁፍ ጥቂቶች ምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴር የአቶ ደመቀ መኮንን ሃይማኖት ሙስሊም መሆናቸውን በመጠራጠራቸው ስለ አቶ ደመቀን ጀርባ እንድንጽድላቸው ጠይቀውን ነበር፤  እኛም ጥቂት ካነበብነውና ከቅርብ ሰዎች ከሰማነው መሰረት በማድረግ  ስለ አቶ ደመቀ ፤ ስለ አቶ ኃይለማርያምና መጽሀፍ በማገላበጥ ስለ ወላይታ ጥቂት ማለት እንወዳለን፡፡

 አቶ ደመቀ መኮንን ተወልደው ያደጉት ምዕራብ ወሎ ማሻ ከተማ ውስጥ ነው ፤ አንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን የተከታተሉት መንታ ውሃ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህር ቤት ነው ፤ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ቻግኒ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተከታትለዋል፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ተምህርት ባመጡት ውጤት በ1974 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሳይንስ ፋካሊቲ  በመግባት  በ1978 ዓ.ም በስነ ህይወት በመጀመሪያ ድግሪን ተቀብለዋል በተጨማሪ በአሜሪካ ሁለተኛ ድግሪያቸውን ሰርተዋል፡፡ አቶ ደመቀ መኮንን በአማራ ክልል የአስተዳደርና የጸጥታ ቢሮ ኃላፊና የፀረ ሙስና ቢሮ ኃላፊም በመሆን ሰርተዋል፡፡ የአማራ ክልል ምክር ቤት የጽ/ቤት ኃላፊ ሆነው ለ4 ዓመታት የሰሩ ሲሆን ከምርጫ 97 በኋላ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደርና የክልሉ የአቅም ግንባታ ቢሮ ኃላፊ ሆነው ለ5 ዓመታት ካገለገሉ በኃላ የብአዴን ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል ፤  በአሁኑ ሰዓት ወደ ፌደራል መንግስት በመዘዋወር የትምህርት ሚኒስቴር ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ፡፡
የልጅ እያሱ አባት ንጉስ ሚካኤል  መሀመድ አሊ ይባሉ ነበር ፤ መሀመድ አሊ ንጉስ ሚካኤል ተብለው የተሾሙት እምነታቸውን ለውጠው ነበር ፤ ወሎ ውሰጥ በሰው ስም የሚከተለው እምነትን መለየት አዳጋች ነው ፤ የአቶ ደመቀ አባት አቶ መኮንን ሀሰን በማሻ አካባቢ የታወቁ አርሶ አደር ናቸው፡፡ እናታቸው ወ/ሮ እታዋ ተፈራ የቤት እመቤት ሲሆኑ አምስት ወንድምና አራት እህቶች አሏቸው ፤ አቶ ደመቀ ለአባታቸው ሁለተኛ ልጅ ናቸው ፤ አቶ ደመቀ ወ/ሮ አለሚቱ አሊን አግብተው ሁለት ወንድና አንድ ሴት ልጅ ከትዳራቸው ማፍራት ችለዋል ፤ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሚማሩበት ወቅት ለክረምት ወደ ቤተሰብ ሲሄዱ በልጅነታቸው እንደሚያደርጉት ቁርዓን በመቅራት እና የአባታቸውን ማሳ በማረስ ጤፍ ፤ በቆሎና ዳጉሳ በመዝራት አባታቸውን በስራ ያግዙ እንደነበር አብረዋቸው ከተማሩ እና በተለያየ ከፍተኛ የመንግስት ስልጣን ላይ ያሉ ሰዎች ይናገራሉ፡፡ ወሎ ውስጥ  በአንድ ቤተሰብ ውስጥ እስልምናና  ክርስትና አማኞችን ማግኝት ቀላል ነው ፤ አቶ ደመቀ በውይይት የሚያምኑ ሰው ናቸው ይባላሉ ነገር ግን በያዙት አቋም ግትርነት የሚያጠቃቸው ሰው ናቸው በማለትም በቅርብ የሚያውቋቸው ሰዎች ይናገራሉ ፡፡  የአቶ ደመቀን ይችን  ካቀረብን ስለ አቶ ኃ/ማርያምና ስለ ወላይታ ጥቂት እንበል፡፡
አቶ ኃ/ማርያም በወላይታ ዞን አረካ በምትባል መንደር ሐምሌ 12 1958 ዓ.ም ተወለዱ ፤ ለእናትና ለአባታቸው የመጀመሪያ ልጅ ሲሆኑ እሳቸውን ተከትለው ስምንት ወንዶችና አንዲት ሴት ልጅ ወደዚች ዓለም ተከትለዋቸው መጥተዋል ፤ አቶ ኃ/ማርያም በ1981 ዓ.ም ትዳር ሲመሰርቱ እሳቸው የ27 ዓመት ጎልማሳ ሲሆኑ ባለቤታቸው ወ/ሮ ሮማን ደግሞ የ22 ዓመት ወጣት ነበሩ ፤ በጋብቻ ውስጥ ሶስት ሴት ልጆችን ማፍራት ችለዋል ፤ አቶ ኃ/ማርያም እና ወ/ሮ ሮማን ሁለት ሁለት ማስተርስ ድግሪ እያንዳንዳቸው እንዳላቸው ይነገራል፡፡ የአቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝ ታናሽ ወንድም ደ/ር ፍቅሬ በአሁኑ ሰዓት የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት ናቸው ፡፡
ወላይታና ንግሥና  …
የፓቶሎሚ(ሞቶሎሚ) የተባለው የወላይታ የሁለተኛው ማላ ሥርወ መንግስት 11ኛ ንጉሥ ኃይለኛ ስለነበረ  ቡልጋ ላይ ዘምቶ  በምርኮ ብዙ ሰዎችን ይዞ ሲሄድ የአቡነ ተክለ ሃይማኖትን እናት እግዚእ ሐርያን በጊዜው ይዞ ሄዶ ነበር ፡፡ “እግዚእ ሐርያን ግን የወታደር ጭፍሮች በማረኳት ጊዜ አክብረው ይዘዋት ሄዱ ፡፡ ለጌታችን ለንጉሡ ሚስት ትሆናለች ብለው፡፡ እጅግ መልከ መልካም ነበረችና”( ይህ  ገድለ ተክለሃይማት ላይ ተጽፏአል ) ፤ እግዚእ ሐርያን ካዎ ፓቶሎሚ ለማግባት አስሞሽሮ ካስቀመጠበት የጣኦት ቤት ቅዱስ ሚካኤል አውጥቷቸው ወደ ቡልጋ ከተመለሱ በኋላ ከባለቤታቸው ከካህኑ ከጸጋ ዘአብ መጸነሳቸውንና አቡነ ተክለሃይማኖት መወለዳቸውን ገድሉ ላይ ሰፍሮ ይገኛል ፡፡
 “ያን ጊዜ ድንገት ከሰማይ መብረቅ በረቀ ፤ ብልጭልጭታ ሆነ ነጎድጓድ ተሰማ ፤ ዓለሙን ሁሉ ተነዋወጠ ፤ ቅዱስ ሚካኤል ወርዶ ከመካከላቸው አንስቶ በክንፉ ታቅፎ ወሰዳት ፤ ከዳሞት ዞረሬም በሶስት ሰዓት ወሰዳት ፤ በመጋቢት በ22 ቀን ጸጋ አብ ከቤተመቅደስ ገብቶ ሲያጥን ለሷ ሲለምን ከቤተመቅደስ አግብቶ ከዚያ ትቷት ወደ ሰማይ አረገ ፤ ከነጎድጓዱና ከመብረቁ ፍርሃት የተነሳ ሞተለሚ ደነገጸ አእምሮውን አጣ” ይላል፡፡ (ገድለ ተክለ ሃይማኖት 12፤136)
ንግሥናና ወላይታ አንድ ሺህ  እድሜ ርዝማኔ አላቸው ፤ በታሪክ ፓቶሎሚ ተብሎ የሚጠራው በገድለ ተክለ ሃይማኖት ደግሞ ሞቶሎሚ የሚባለው ንጉሥ እዚው ቦታ ነግሶ እንደነበር ይነገራል ፤ ወላይታና አካባቢዋ በንጉሥ መተዳደር የጀመረችው ከአስርት መቶ አመታት በፊት ነበር ፤ በጊዜው ነገሥታት ካዎ የሚል ቅድመ መጠሪያ ነበራቸው ፤ ካዎ ማለት በወላይትኛ ንጉሥ ማለት ሲኾን ቡሻሻ ማለት ደግሞ አልጋ ወራሽ ማለት ነው ፤ ወጋ ማለት ትልቅ ወይም ኃይለኛ ማለት ነው፡፡ እንዲሁም ጦሶ ማለት እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ስንተኛ ካዎ እንበላቸው?
የወላይታ ስርወ መንግስት ከ10ኛው እስከ 1553ዓ.ም ድረስ ካዎ ፓቶሎሚ(ሞቶሎሚ)--›ካዎ ታላሜ ---› ካዎ ማካስ --› ካዎ ሞታ--› ካዎ ሞቼ---› ካዎ ላቼ እንደነበሩ ታሪክ ይናገራል፡፡ የካዎ ላቼ መንግስት ስለደከመ ከተንቤ ለመጣ ጦረኛ ለሹም አጋሜ በጋብቻ ከተሳሰሩ በኋላ መንግስቱን በ1553 ዓ.ም ለቀቁለት ፤ ከካዎ ላቼ በኋላ ካዎ ሚካኤል--› ካዎ ግርማ --› ካዎ አዳዮ--› ካዎ ኮቴ በዘመን በመቀያየር ወላይታን አስተዳድረዋል ፤  ካዎ ኮቴ የትንቢት ንጉሥ ይባል ስለነበር  “ከእኔ 10ኛው ትውልድ መንግስት ከዘሬ ይወጣል” ብሎ ተንብዮ ነበር ይባላል፡፡ የካዎ ኮቴ አስረኛ ዘር በንጉሥ አጼ ሚኒልክ ጊዜ ኢትዮጵያ አንድ ሳትሆን ሁሉም በግዛቱ ላይ ንጉስ በሚባልበት ዘመን  የነበሩት ካዎ ጦና ነበሩ፡፡ ካዎ ጦና በ1882 ዓ.ም የንግስናውን ወንበር ያዙ ፤ ካዎ ጦና ነግሰው 5 ዓመት ሳይሞላቸው በ1887 ዓ.ም ከሚኒሊክ ጋር በተከሰተ አለመግባባት ጦር ገጥመው በሚኒሊክ ስለተሸነፉ የመጨረሻው የወላይታ ንጉስ ኾኑ ፡፡ ሚኒሊክ ሀገሪቱን አንድ ለማድረግ በተነሱበት ወቅት እሺ ያለውን በሰላም ሲያቀላቅሉ እምቢ ያለውን ደግሞ ጦር ይጠቀሙ እንደነበር የታሪክ ድርሳናት ይናገራሉ ፤ እምዬ ሚኒሊክ ንጉስ ጦና ጀግና በመሆናቸው ለንጉስ የሚደረገውን ክብር በመስጠትና ባለመንፈግ ወደ አዲስ አበባ እንዲመጡ ካደረጓቸው በኋላ  እጅግም ስላከበሯቸው የክርስትና አባት ኾነው መልሰው የወላይታ አገረ ገዥ አድርገው ሾመዋቸዋል ፡፡ ከዚያን ጊዜ በኋላ የካዎ ጦና የልጅ ልጆች ከሸዋ መኳንንት ልጆች ጋር በጋብቻ የተሳሰሩም ነበሩ ፤ ይህ ማለት የካዎ ጦና ዘር የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ በመሆናቸው ከመኳንንት ልጆች ጋር ጋብቻ መፈጸም ይችሉ ነበር ማለት ነው፡፡
ንጉሥ ጦና ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩ አዲስ አበባ በዓለ ወልድ ቤተክርስቲያን አስከሬናቸው አርፎ በአሁኑ ወቅት መቃብራቸው በቤተክርስቲያኑ መግቢያ በስተቀኝ በኩል ይገኛል ፤ ከዚያን ጊዜ በኋላ የወላይታ ህዝብ የፕሮቴስታንት ንፋስ እጅጉን ከመንፈሱ ቀድሞ አብዛኛው ክፍል የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ ነበር ፤ በ20ኛው ክፍለ ዘመን የምዕራባውያን ስልጣኔ ገፍቶ የመጣበት ወቅት ስለነበረ ኢትዮጵያ በሃይማኖት ጭቅጭቅ ምክንያት ዘግታ የነበረውን በሯን  የምዕራባውያንን ስልጣኔ ፍለጋ ለመክፈት ተገደደችበት በመሆኑ ፤በዚህ ምክንያት ብዙ የምዕራባውያን ኃይማኖቶች በይፋ ወደ ሀገራችን የገቡት መሰረታቸውንም የጣሉት  ዘመነ መንግስትም መሆኑ ይታወቃል ፡፡ (ሃይማኖቶቹ በአሁኑ ሰዓት በ2004ዓ.ም የሃይማት ፍቃድ እደሳ መሰረት በቁጥር ከ178 አልፈዋል ..)
ከላይ እንደተገለጸው ወላይታን በዘመናት ከፓቶሎሚ(ሞቶሎሚ) ጀምሮ እስከ ንጉስ ጦና  ድረስ 20 ነገስታት ተፈራርቀው የነገሱባት ሲሆን ሁሉም ወላይታና አካባቢውን ማስተዳደር ችለው ነበር ፤ ከንጉስ ጦና በኋላ አዲሱ ካዎ በአሁኑ ሰዓት በዘመናዊነትን ብቅ ብሏል ፤ አሁን በዘመን ሂደት በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በ2005  ዓ.ም መስከረም በባተ  በአስራ አንደኛው ቀን አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝ ለቀጣይ 3 ዓመት ኢትዮጵያን ለማስተዳድ የሀገሪቱን ከፍተኛ የስልጣን ቦታ ባልታሰበ ሰዓትና ጊዜ የቀድሞውን የአቶ መለስ ዜናዊን ድንገተኛ ሞት ተከትሎ የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ቦታ ተረክበዋል፡፡ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝን ስንተኛ ካዎ እንበላቸው?
በሶስት ትውልድ ሶስት ሃይማኖት
የአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስቴር የአቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝ አያትም በጊዜው የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ መሆናቸው የቅርብ ሰዎች ሲናገሩ ፤ አባታቸው አቶ ደሳለኝ ደግሞ የቀድሞው እምነት በመተው የካቶሊክ እምነት ተከታይ ነበሩ ፤ በጊዜው  አቶ ደሳለኝ ቦሼ የሶዶ ቅድስት ማርያም ካቶሊክ ትምህር ቤት መምህርና ዳይሬክተር መሆናቸው ይነገራል ፤ የአቶ ደሳለኝ ልጅ አቶ ኃ/ማርያም ደግሞ የONLY JESUS(ሐዋርያዊት) የእምነት ተከታይ ናቸው ፤ የአቶ ኃ/ማርያም ልጆቻቸው በአሁኑ ወቅት የአባታቸውን እምነት ሲከተሉ ፤ ነገ  ከየትኛው ጎራ እንደሚገኙ እርግጠኛ ሆኖ መናገር አይቻልም ፤ ወይ አራተኛውን እምነት ይቀበሉ ይሆናል ፤ ያለበለዚያ ደግሞ የአባታቸውን እምነት በሶስተኛው ሊጸኑም ይችላሉ ፤ በሶስት ትውልድ ሶስት አይነት ሃይማኖት፡፡

Washington DC & SON OF WOLAITA’S KING
የካዎ ጦናን ልጅ ቡሻሻ ሮቤ(ሕዝቡ ፍስሐ ጦና  ብሎ ይጠሯቸው ነበር) የንጉስ ልጅ ቢሆኑም የአባታቸውን ወንበር ግን አልነገሱበትም ነበር ፤ የእሳቸው ልጅ ፊታውራሪ ደስታ ፍስሐ ይባላሉ ፤ ፊታውራሪ ደስታ የሸዋ መኳንንት የአዛዥ ሽብሩን ልጅ አግብተው አምስት ልጆች ወልደዋል ፤ ፊታውራሪ ደስታ ፍስሐን ሰዎች ደስታ ጦና በሚል ስም ይጠራቸው ነበር ፡፡ አሜሪካን አገር ሄደው ስለሞቱ አስከሬናቸው እዚያው በአሜሪካ አገር ቨርጂኒያና ዋሽንግተን ዲሲ መካከል በሚገኝው ግሬት ፓቶማክ ወንዝ አጠገብ ከቀድሞ ፕሬዝዳንት ዊድሮው ዊልሰን መቃብር ቁጥር 2176 አጠገብ አርፏል ፡፡ ቁጥር 2146 መቃብራቸውም ላይ    “SON OF WOLAITA’S KING” የሚል ጽሁፍ ተጽፎበታል፡፡
የበይ ተመልካች
ባለፈው ጽሁፋችን ስለ ጠቅላይ ሚኒስተር ሹመትና እምነትን መሰረት አድርገን ጽፈን ነበር ፤ አሁንም ከዛው ሳንወጣ ትንሽ ለማስዳሰስ ሞክረናል ፤ አሁን የኛ ፍራቻ ወንበሩን እነርሱ ሲፈራረቁበት እኛ የእነሱን ታሪክ ጸሀፊና አንባቢ ሆነን እንዳንቀር ብቻ ነው፡፡ ለልጅ ልጆቻችን የሌሎችን ታሪክ ተናጋሪ ሆነን እንዳንገኝ ባለንበት ፤ በኖርንበትና በምንኖርበት ዘመን ለራሳችንና ለቤተክርስትያናችን ታሪክ እንድንሰራ እግዚአብሔር ይርዳን፡፡ 
ቸር ሰንብቱ 
ግብዓት
  • ·        የ20ኛው ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያ(ጥላሁን ብርሃነ ሥላሴ ቤተ)
  • ·        ገድለ ተክለ ሃይማኖት
      Our Best Blog check it:- (http://www.ermiasnebiyu.blogspot.com/
http://mekrez.blogspot.com/ )

6 comments:

  1. wow Andadren

    We are very proud of you guys , This is well organised ,true , and even details sources, excellent well done. We like you guys ,
    May GOD bless u all.

    I was so amazed you mentioned even the no where he was buried, I hope the prime minister has to pay visit. This is realy good history. But the prime minister may no idea about this at least his daughters might read and tell him.

    አሜሪካን አገር ሄደው ስለሞቱ አስከሬናቸው እዚያው በአሜሪካ አገር ቨርጂኒያና ዋሽንግተን ዲሲ መካከል በሚገኝው ግሬት ፓቶማክ ወንዝ አጠገብ ከቀድሞ ፕሬዝዳንት ዊድሮው ዊልሰን መቃብር ቁጥር 2176 አጠገብ አርፏል ፡፡ ቁጥር 2146 መቃብራቸውም ላይ “SON OF WOLAITA’S KING” የሚል ጽሁፍ ተጽፎበታል፡፡

    ReplyDelete
  2. Thank you for your information. But please put the right birthplease of the vpm. Where is mierab wollo? There is some information that he is from 'agewawi' zone.

    ReplyDelete
  3. Thank you for your information. But please put the right birthplease of the vpm. Where is mierab wollo? There is some information that he is from 'agewawi' zone.

    ReplyDelete
  4. Betamm Yegeremegnn negr lemehonu Egziaeher Sewn hulu Be 1 ayentbota new meyayew eanete gin yetsafachuten tasetewelalachehu?? Egziabeher dawiten keyet new yeteraw Egziabeher yefeerewen sew ezhi geba yemayebal yilal ? blogu ye keresteyan ayemeselem yepoletika enji mikeneyatum Egziabeher yewedekutin yemeyanesa amelak mehonun yawekacehu alemeselegnem setetsefu asetewelachu leanebabeyan akerbu mechem enedmetawetut asteyayeten amenalhu katefahum yikerta yetwahedo lij negn Egziabeher yeredan

    ReplyDelete
  5. Yetemare yilishal yihe new...aba selama yetebalew ye alubalta web site sile enante day and night yisefal ennate demo....you every time provide up to date and useful information, which is very important for all of us, even for them selves. By far being better malet yihe new. Go ahead please ...we always support you and can't wait till you post us another time. All of your articles contain helpful and important information. If you were not there and defend our church "tehadiso" yachin church afrso neber. God bless you!!

    ReplyDelete
  6. አንድ አድርገኖች በተከታታይ ጽሁፋችሁ የወቅቱን መሪዎቻችንን የትውልድ ማንነትና ሃይማኖት ፣ የፖለቲካ አመለካከትና አቋማቸውን ለማስገንዘብ ብዙ ጽፋችኋል ፡፡ በዲሞክራሲ በአደጉት ፣ እንደ አሜሪካ ባሉ አገሮች የመሪዎች ማንነትና ምንነት በአብዛኛው ተበታትኖና ተንጠርጥሮ የሚታየው ለምርጫ በሚቀርቡበትና ፣ የምረጡኝ ቅስቀሳ በሚያካሂዱበት ሰዓት ነው ፡፡ ምክንያት ቢሉ የአመራሩን ወንበር ለመቆናጠጥ የማያበቃ ድክመት ከተገኘ ፣ ከወዲሁ ከመንገድ ለማስቆምና ለማባረር ስለሚረዳቸው ነው ፡፡ ይህንንም ታሪክ በተግባር መፈጸሙን ለመረዳት በየጊዜው በበቃኝ ከውድድር የወጡትን ተወዳዳሪዎች ቁጥር ማየቱ በቂ ነው ፡፡

    ምክንያቶቹ ደግሞ ከትዳር ውጭም ሆነ በወጣትነት ሴትን ማባለግ ፣ በሥልጣን አላግባብ መጠቀም ፣ ቤተሰብን በአግባቡ አለመምራትና አለመንከባከብ ፣ ታማኝነትን ማጉደል ፣ ያለ አግባብ ከህግ ውጭ ገንዘብን መሰብሰብ ፣ ለመንግሥት የሚፈለገውን ግዴታ ፈጽሞ አለመገኘት ፣ የአደገኛ ዕጽና አልኮሆል ሱሰኝነት ፣ ለሃገርና ለወገን ጥቅም ዘብ ሆኖ አለመገኘት ፣ የሥነ ምግባር ደካማነት ፣ …………. ናቸው ፡፡ ብቻ ድክመት የሚባሉት ነገሮች ሁሉ ተቆጥረውና ተዘርዝረው አያልቁም ማለቱ ይቀለኛል ፤ የነገሮቹም ክብደት ደግሞ የሚመዘነው በመደጋገማቸው ሳይሆን ፣ አንድም ቢሆን እንኳን በቂ ማስረጃ ከተገኘበት ፣ ግለሰቡን ለመነዝነዝና ለማባረር እጅግ ትልቅ ነው ፡፡

    የአሁኑ ኘሬዘዳንት እንኳን በወቅቱ ቀርበውባቸው ከነበሩት ከባድ ጥያቄዎች መካከል ከአሜሪካ ግዛት ውጭ የተወለዱ ናቸውና ፣ በዜግነታቸው ምክንያት ፣ ሃይማኖታቸው በወላጅ አባታቸው ዘር በኩል እስልምና ስለሆነ የእሳቸውም እምነት አክራሪ እንዳይሆን ፣ ከአሜሪካ ተቀናቃኝ ግለሰቦችና ድርጅቶች ጋርም ኀብረትና አንድነት ነበራቸው የሚልም ዶክመንታሪ ሁሉ ቀርቦባቸው ነበር ፤ ነገር ግን ለሁሉም አግባብ ያለው ማስረጃና ሰነድ አቅርበው ፣ በቃላቸውም አስረድተው መሰናክሎችን አልፈው ለዚህ ላሳለፉት ዓመታት የሥልጣን ዘመን በቅተዋል ፡፡ ይህን እንዳይመረጡ ማጣራት የሚያደርገው ደግሞ ያጫቸው ፓርቲ ደጋፊ ኀብረተሰብና እንዳይሸነፉ የሚፈልገው ፓርቲአቸው ፣ ለማሸነፍና የራሱን ለማስመረጥ በሚል ምክንያት የሚታገላቸው ተቃዋሚው ፓርቲ ፣ የመንግሥትም የጸጥታና የደኀንነት ክፍል ሁሉ ነው ፡፡ በሃገራችን ግን ልምዱ ስለሌለ ፣ ግለሰቦችም በምርጫ ሳጥን በተገኘ ውጤት ወደ ሥልጣን እርካብ ስለማይመጡ ፣ ባንዲራችንን ጨርቅ (አህያ የምትለብሰው) የሚልና ህጻናት የሚያውቁትን አረንጓዴ ቢጫ ቀይነቱን እንኳን የማይጨነቅለት (http://tassew.files.wordpress.com/2012/06/melee_anti-ethio_flag.jpg?w=600&h=450)
    ፣ አገርንና ህዝብንም ጨምላቃና ቁሻሻ ፣ ብስባሽ ፣ እያለ የሚሰድብ መሪም አስተናግደናል ፡፡

    ሌላው ነጥብ ደግሞ ይኸ ከላይ የተጠቀሰው መሠረታዊ የሥልጣን ኮርቻ ላይ አወጣጥ ደንብና ሥርዓት ስለሌለን ፣ እናንተም ጅብ ከሄደ ውሻ ጮኸ እንዲሉ ፣ ነገሮች ከተደመደሙ በኋላ ነው የሰዎችን ማንነትንና ያለፈ ታሪካቸውን ለማጥናት የሞከራችሁት ፡፡ ስለዚህም ዲሞክራሲ በተግባር ባልተገለጸበት አገር የግለሰቦቹን የህይወት ገጠመኝ ማወቁ ጥቅሙ እጅግም ጎልቶ አልታየኝም ፡፡

    ይህን በማለቴ ግን የሠራችሁት ሥራ ፈጽሞ ጥቅም የለውም ፣ ዋጋ ቢስ ተራ ወሬ ነው የሚል አቋም የለኝም ፡፡ እንዲያውም ማንነታቸውን በተቻለ መጠን ካወቅን ፣ ወደፊት የሚሠሩት ሥራና የሚያስመዝግቡን ውጤት ከዚሁ ከማንነታቸው ጋር ይቆራኝ እንደሁ ለመፈተንና ለመከታተል የበለጠ ይረዳናልና ፣ ከዚህ በኋላ ያለው ጽሁፍ በየጊዜው በሚያወጡት የሥራ መመሪያ ፣ ለአገርና ለህዝብ የኑሮ ዕድገት የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ፣ ለኀብረተሰቡም ሰላምና ሙሉ ነጻነት ለማጎናጸፍ በሚያሳዩት ቁርጠኛ ትግል ላይ ትኩረት ቢደረግ መልካም ነው እላለሁ ፡፡

    ReplyDelete