Tuesday, July 22, 2014

“ኦርቶዶክስን መሳደብ ማለት እናቴን እንደመሳደብ እቆጥረዋለሁ” አርቲስት ጥላሁን ጉግሳ


(አንድ አድርገን ሐምሌ 15 2006 ዓ.ም)፡- ከዓመታት በፊት በተሰራ አንድ ድራማ ላይ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነትን ፤ የእምነቱን አባቶችና ፤ ቤተ ክርስቲያኒቱ ያከበረቻቸው ጻድቃን ሰማዕታት ላይ የሚሳለቅ ድራማ በመስራት ለሕዝብ አቅርቧል በማለት ስሙ የሚነሳው የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ የሆነው አርቲስት ጥላሁን ጉግሳ እና ድራማው ላይ የተሳተፉ የሙያ ባልደረቦቹ በምዕመናን ዘንድ በተፈቀደ መድረክ ቤተክርስቲያኒቱን የማይመጥን ፤ ከስድብ ባለፈም አባቶች ላይ የሚያላግጥ ድራማ ነው በማለት ሰዎች ቅሬታቸውን ሲያሰሙ እንደነበር ይታወቃል፡፡(የድራማውን አንዱን ክፍል ይመልከቱ )፡


ይህን በተመለከተ ከሎሚ መጽሔት ጋር አርቲስቱ ቃለ ምልልስ ሰጥቶ ነበር፡፡ ቃለ ምልልሱን እነኾ…..

ሎሚ ፡- የሙያህ አድናቂዎችህና አፍቃሪዎችህ እንዳሉ ሁሉ አንዳንዶች ደግሞ ቅሬታ ያላቸው አሉ..
ጥላሁን ፡- ቅሬታ ስትል ምን ማለትህ ነው? ከሙያህ ጋር በተገናኝ ነው ወይስ በግል ? አልገባኝም

ሎሚ፡- ቅሬታ አቅራቢዎቹ አንድ ድራማ ላይ ስለ ኦርቶዶክስ አባቶች የማይገባ ንግግር ተናግረሃል በሚል ነው፡፡
ጥላሁን፡- ይህ የተባለው ድራማ የተሰራው በ1993 ዓ.ም ነው፡፡ ይሁንና ከ13  ዓመት በፊት ቢሆን በማንም ላይ ያልተገባ ንግግር መናገር አለብኝ ብዬ በጭራሽ አላምንም፡፡ አልተናገርኩምም፡፡
ሎሚ፡- እንደውም ‹‹ የኦርቶዶክስ አባቶች ገዳዳ ነገር ይዘው ትውልዱን አንጋደዱት›› ብለሀል ነው የተባለው፡፡
ጥላሁን ፡- ፈጽሞ ስህተት ነው፡፡ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቀደምትና ከክርስቶስ ልደት ጀምሮ ኢትዮጵያ እንደ ትውልድ ጠብቃ ያስረከበችን ሃይማኖት ናት፡፡ እኔም ሆንኩኝ ሌሎቻችን የተገኝነው ከኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ነው፡፡ በአጠቃላይ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የታሪካችን ፤ የባሕላችን ፤ የማንነታችን  መነሻ መሰረት ነው፡፡ እኔም ራሴን ከዛፍ ላይ የተሸመጠጥኩ  ሳይሆን ከኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት የተገኝሁ ነኝ፡፡ ለእኔ ኦርቶዶክስን መሳደብ ማለት ወልዳ ያሳደገችኝን እናት እንደመሳደብ ያህል እቆጥረዋለሁ ፤ ሰው እናቱን ይሳደባል? በጭራሽ…
ሎሚ ፡- ታዲህ ይህ ነገር ከየት መጣ ?
ጥላሁን ፡- የዛሬ 13 ዓመት የተሰራን ድራማ አንስተው ልክ ዛሬ እንደሆነ በማስመሰል ፤ በጭራሽ ያላልኩትን ‹‹አለ›› እያሉ… እኔን ከሕዝቡ ጋር ለማጋጨትና ስሜን ለማጥፋት የሚሞክሩ ጥቂት ሰዎች ያቀነባበሩት ተንኮል ነው፡፡ እነዚህ ግለሰቦች የተለየ ፍላጎትና አላማ ያላቸው ናቸው፡፡ .. ያም ሆኖ የኦርቶዶክስ አባቶችና ሊቃውንቶቹ ይህንን ድራማ አይተው “ይህን የሚመስል ነገር አለው” ካሉኝ ለመታረምና በይፋ ይቅርታ ለመጠቅ ዝግጁ ነኝ፡፡
ሎሚ ፡- ድራማው ላይ እኮ ‹‹ትውልዱን ያጋደድነው እኛ ነን›› ብለሃል፡፡

ጥላሁን ፡- ያ ማለት በድራማው በተፈጠረው ታሪክ ላይ ሁለት ውጭ ያሉ አባቶች ሲነጋገሩ ትውልዱን አንጋደድነው ብለው ስለ ራሳቸው አባትነት ነው እንጂ የሚናገሩት  ፈጽሞ የኦርቶዶክስ አባቶች አይልም፡፡ ሰው ያላለውን አለ በማለት ነገር እየሰነጠቁ በውሸት መክሰስና ስም ማጥፋት እግዚአብሔም የሚወደው ነገር አይደለም፡፡ ደግሞም ኢትዮጵያ የሃይማኖት እኩልነት ያለባትና ሃይማኖቶች ተቻችለው የሚኖሩባት ሀገር ናት፡፡ ሃይማኖት የግል ነው፡፡ አገር የጋራ ነው እንደሚባለው ፤ ሰው የፈለገውን ሃይማኖት የመከተል መብት አለው ፡፡ ይህ ሲሆን የሌላውን እምነት ማክበር ግድ ነው፡፡ እኔ ግን በግሌ ክርስቲያን ክርስቲያን ነው ብዬ ነው የማምነው፡፡

አርቲስት ጥላሁን  : ቆም ብለህ ተመልክ ቤተ ክርስቲያን ይቅርታ ጠይቅ 

አዎን እዚች ሀገር ውስጥ ማንም የፈለገውን ሃይማኖት የመከተል መብት አለው፡፡ በድንጋይም ፤ በውሃም ሆነ ኦና በሚያድር የቆርቆሮ አዳራሽም አምልኮትን መፈጸም ይቻላል ፤ እዚች ሀገር ማምለክ ብቻ ሳይሆን ምንንም አለማምለክም መብት ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ሕጋዊ ፍቃድ በሌለው አኳሃን መንገድ ላይ ‹‹ወንድሜ አንዴ ላናግር..›› እያሉ የሃይማኖት አስተምኸሯቸውን ማሕበረሰቡ ላይ የሚጭኑበት ሀገር ላይ ነው የምንገኝው፡፡ የሃይማኖት እኩልነትን የሚደነግገው ሕገ መንግስት መሰረትም ከ180 በላይ በክርስትና ስም ብቻ የሃይማኖት ተቋማት የተቋቋሙበት ሀገር ላይ ነው የምንገኝው፡፡ ይህ ሁሉ ሆኖ ሳለ ቀደምት የታሪክ ፤ የትውፊት እና የእምነት መሰረት ለሀገሪቷ አንድነት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳትል የባሕር በሯን ከድንበሯ ሳትለይ ሀገሪቱ ሀገር እንድትሆን ያደረገች ፤ በስድስተኛው ክፍለ ዘመን ከአረብ ሀገር ተሰደው የመጡ የእስልምና እምነት ተከታዮችን ተቀብላ ያስተናገደች ለዛሬ ማንነታቸው መሰረት የጣለች ቀደምት የመጀመሪያ የሆነች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንም የምትገኝበት ሀገር ነው የምንገኝው፡፡ ስለዚህ ብዙ ብሔር ፤ ብዙ ቋንቋ ፤ ብዙ ሃይማኖት እያስተናገደች ባለች ሀገር በሕዝቦችና በእምነቶች መካከል ለሚኖር ሰላም መሰረቱ በእምነቶች መካከል የሚፈጠር የእርስ በእርስ መልካም ግንኙነትና ፤ የመከባበር ባሕል ነው፡፡

ይህ እንዲህ ሆኖ ሳለ አርቲስት ጥላሁን የዛሬ 13 ዓመት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ለስርዓተ አምልኮ የምትጠቀምባቸው ከመጽሐፍ ቅዱስ ያላፈነገጡ ገድላትንና ድርሳናትን ተረተረት ከማለት በተጨማሪ ‹‹ያለ ብልሀት የተፈጠረ ተረት›› በማለት በመጻሕፍቱ ላይ ተሳልቋል፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱ በሰሩት ሥራ መዝና የሰማዕትነትና የጻድቅነትን ስም በመስጠት በስማቸው ታቦታትን የቀረፀችላቸው ለመንበረ ፕትርክና መጠሪያ ያደረገቻቸውን ቀደምት አባቶቻችንን ጻድቃን ሰማዕታት ላይ አፍ አውጥቶ በአሽሙር ከመዝለፍና ከመናገር በተጨማሪ ክብራቸውን በማሕበረሰቡ ዘንድ ዝቅ የሚያደርግ ድራማ ሰርቷል፡፡

ይህ ሰው ይህን ብቻ አይደለም ያደረገው ለሰሚው የማይመች ቃላትንም በጎልማሳነት ዘመኑ ተናግሮ ከእምነቱ ተከታይ ወጣቶች ጋር በግልጽ ተጋጭቷል፡፡ ይህን ሁሉ አድርጎ ካበቃ በኋላ ዛሬ ላይ በሰከነ በሚመስል እድሜው የሰራውን ሥራ ይቅርታ በማለት ቤተ ክርስቲያኒቱን በሚጠይቅበት ሰዓት በፍጹም አልሰራሁም ፤ አላደረኩም ብሎ አይኔን ግንባር ያድርገው ማለቱ እጅግ ያሳዝናል፡፡

አንድ የድራማ ስክሪፕት ሲጻፍ የማሕበረሰቡን መልካም እሴት እንዳይንድ ፤ የሰዎችን የሃይማኖት አመለካከት እና እምነት ላይ  ዝቅ እንዳያደርግ ፤ የሀገሪቱን መልካም ገጽታ እንዳያበላች ፤ በብሔር ብሔረሰቦች መካከል ቂም እንዳያስቋጥር በጠቅላላ ሃይማኖታዊ ፤ ባሕላዊ ፤ ማሕበረሰባዊ እና ሀገራዊ ጉዳዮችን እንዳያንቋሽሽ ተደርጎ ነው ለሕዝብ መቅረብ ያለበት፡፡ አርቲስት ጥላሁን ጉግሳ በጊዜው ያደረገው ነገር ግን ተደማጭነቱን ብቻ ተገን በማድረግ ዛሬም ‹‹አላደረኩም እንዲህ ለማለት ፈልጌ አይደለም›› ብሎ ሸምጥጦ በመካድ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶን እምነት ፤ ትውፊት ፤ ስርዓተ አምልኮ መፈጸሚያ መጻሕፍትን ፤ ጻድቃን ሰማዕታት ላይ ተሳልቋል፡፡

አርቲስቱ ‹‹በጭራሽ ያላልኩትን ‹‹አለ›› እያሉ… እኔን ከሕዝቡ ጋር ለማጋጨትና ስሜን ለማጥፋት የሚሞክሩ ጥቂት ሰዎች ያቀነባበሩት ተንኮል ነው፡፡ እነዚህ ግለሰቦች የተለየ ፍላጎትና አላማ ያላቸው ናቸው፡፡›› ብሏል፡፡ ቤተ ክርስቲያን በዚህ ሰው አማካኝነት ክብሯ ተነክቷል ያሉ ምዕመናን ከሺህ በላይ አርቲስት በሚገኝበት ሀገር የተለየ አላማ እና ፍላጎት እንዴት በአንድ አርቲስት ላይ ብቻ ይኖራቸዋል? ሰው ስሙ የሚጠፋው በስራው ነው ፤ ስሙንም አስከብሮ የሚቆየው በስራው ነው ፤ በአንድ ለሊት የሚገነባ ስም እንደማይኖር ሁላ በአንድ ለሊትም የሚጠፋ ስም አይኖርም፡፡ አርቲስት ጥላሁን አሁንም ሰዓቱ አልረፈደም የሰራሃቸውን ስህተቶች ቆም ብለህ ተመልክተህ ቤተ ክርስቲያንን ይቅርታ ጠይቅ ፤ የቤተክርስቲያን የየቅርታ በር መቼም አይዘጋም፡፡


 (ወደፊት ሙሉውን ድራማ ፖስት የምናደርገው ይሆናል)

18 comments:

  1. ጥላሁ ጉግሳ በራሱ እምነት ውስጥ ሕግን መሠረት አድርጎ የፈለገውን ማለት እነደሚችል ማንም ያውቃል፡፡ ይሁን እንጂ ከአስር ዓመት በፊት የተናገርኩትን እያነሱ ስም ማጥፋት የፈለጉ ሰዎች ያቀረቡብኝ ክስ ነው በማለት የተናገረው ንግግር ሁለተኛ ስህተትና ቤተ ክርስቲያናችንን መናቅ ይመስለኛል፡፡ እነ አቡነ ተክለኃይማኖትን ከመሳደብ በላይምን ድፍረተ አለና!
    ጥለ፤ሁን ጉግሳ (ምናልባት ይህንነ ብሎግ የምታነብ ከሆነ) እስከ ዛሬ ድረስ ስድብህ አልገባን ብሎ፣ ብዙዎቻችን ሳናየው ቀርተን የማናውቀው ሆኖ ወይንም ፈረተን ትተነው አይደለም፡፡ ሁላችንም ስናየው ርባና ቢስ የሆነ ሥራ ስለሆነ በዚህ ጊዜ ማጥፋት እናንተን መምሰልና ጊዜ ማቃጠል ስለሆነ እንዲሁ ስለተውነው ነው፡፡ አሁን ግን የበዛ አልመሰላችሁም? ይብቃ እንጂ ተው! ስለ እግዚአብሔር ብላችሁ (አንተና መሰሎችህ) ተውን! እኛ’ኮ ትተናችሁ መሆኑን መናገር ያለብን አይመስለኝም፡፡ መቀለድ ዋጋ እንደሚያሰከፍል ቢታወቅ ግድ ነው፡፡ አንተ አንደምትለን በአውሮፕላን ጣቢያ ሰዎችን የምንገደል ሳንሆን ምናልባት ከሃይማኖት ባለፈ (አባቶቻችን መንፈስ ቅዱስ ጸፍቶ ያናግራል እነዲሉ) አንተ እንደተነፈስከው ለሃገርና ለወገን የምትሠራ ቤተ ክርስቲያን አለችን፡፡ ታዲያ ነፍሰ ገዳይ፣ ለሥራ ትጋት እንቅፋት የሆነች እያደረጋችሁ አቀረባችኋት!
    አሁንም እኛ የአንተን ውድቀት ሳይሆን ትንሳዔህን የምንመኝ መሆናችንን ላረጋግጥልህ እወዳለሁ፡፡ ጡቷን ጠብተው ካደጉ በኋላ የሚነክሷትን መክራና ዘክራ ሲመለሱ አሁንም ጡቷን ለማጥባት ዝግጁ የሆነች እመቤት (ቤተ ከርስቲያን) ዛሬም በሯ ክፍት ነው፡፡ ይቅርታ ጠይቃት፣ ተመለስ፣ እግዚአብሔር የቀደመውን ማንነትህን ቀይሮ ሰው ለመሆን ያበቀሃል፡፡ ያለህበት ሕይወት እንደማያዋጣህ በእርግጠኝነት እንደምታውቀው አሁኑኑ ውስጥህ ይነግርሃል፡፡ በሕይወትህም በሚገጥሙህ ችግሮች ብዥታው እንዳለብህ አንተና መድኃኔዓለም ትውቁታላችሁ፡፡ የዚህ ሁሉ መፍትሄው አንተ እነዳልካት የሰደብሃትን ቤተ ክርስቲያን ይቅርታ በመጠየቅ እግዚአብሔርን ማስደሰት ነው፡፡ በአንተ መመለስ ሁላችንም ደስ ይለናል፡፡
    ኦርቶዶክሳውያን በሙሉ በአንድ ሰው መመለስ የሰማይ መላዕክት ሁሉ እጅግ ደስ ያለቸዋልና ወንድማችን በመሳሳቱ አንፍረድ፣ ይልቁንስ ለንስሃ በቅቶ ቤተ ክርስቲያንን ይቅርታ ጠይቆ ወደቀደመ ቤቱ እንዲመለስ በጸሎት ማሰብ ተገቢ ነው፡፡ እር የተናገራቸውን ንግግሮች እያደመጥን አንድም የጥላቻ መንፈስ ሊያድርብን አይባም፡፡ ንግግሩን የተናገረው ጥላሁን ጉግሳ ሳይሁን በወቅቱ አብሮት የነበረው መንፈስ መሆኑን መርሳት አይገባም፡፡
    ጥላሁን በርታ፣ ና… ወደ ቤትህ ግባ፤ ና…..! ወደ ቤትህ ግባ!
    የቅዱስ ጊዮርጊስ አምላክ ጥላሁን ጉግሳን ወደ ቀደመ ቤቱ እንዲመልስልን ቅዱስ ፈቃዱ ይሁን፡፡ አሜን!

    ReplyDelete
    Replies
    1. አሁንም ቤቶች ድራማ ላይ በጾም ሲያላግጥ ነበር ትርፌን ድከሚ ሲሊሽ እኮ ነው እያለ ሰውዬው ጤነኛ አይመስለኝም የ666ቱ ሊሲፈር ሰፍሮበታል እግዚአብሔር ይርዳው

      Delete
    2. EWUNET LEHAYMANOT TEKORKUARI KEHONACHU YENEN SEHUF MAWUTAT ALEBACHU.

      Delete
  2. አርቲስት ጥላሁን : ቆም ብለህ ተመልክት ቤተ ክርስቲያንን ይቅርታ ጠይቅ

    ReplyDelete
  3. ቤተ ክርስቲያንን ይቅርታ ጠይቅ ፤ የቤተክርስቲያን የየቅርታ በር መቼም አይዘጋም፡፡

    ReplyDelete
  4. አላወቂ ሰሚ . . . . . አሉ።ወንጌል እንዴት እንደሆነ ስላልገባቸው ነው እንዲ ያሉት። እግዚአብሔር ልቡና ይስጣቸው እላሎሁ

    ReplyDelete
  5. ከመሥሳደቡ መዋሽቱ

    ReplyDelete
  6. አሁንም ቤቶች ድራማ ላይ በጾም ሲያላግጥ ነበር ትርፌን ድከሚ ሲሊሽ እኮ ነው እያለ ሰውዬው ጤነኛ አይመስለኝም የ666ቱ ሊሲፈር ሰፍሮበታል እግዚአብሔር ይርዳው

    ReplyDelete
  7. ምነው አንርሳ እንጂ—በድራማው ላይ ሳይጐብጥ ጐብጦ በያዛት ከዘራ ከላይ ታች እየተመፃደቀ "የግቢ ገብርኤል ነው?ወይስ የቄራው ገብርኤል እያለ በሀይማኖታችን፣በእምነታችን ሲዘብትና ሲያበሻቅጥ እንዳልነበረ አሁን ምን ታይቶት ነው የሚዘባርቀው? መናፍቃን እነ ቦንኬ ፊት ነሱት እንዴ?ቅዱስ ገብርአል ፍርዱን ያሳየን!!!!ይህንን በቅርብ በነበልባላዊ ሰይፉ ፍርዱን ይስጠው።ከበፊቱ ስህተቱ የሰሁኑ ባሰ።

    ReplyDelete
  8. ψጥላሁ ጉግሳ የተሳዳቢ ምላስ ያለው ብቻ ሳይሆን በመድረክ ፕሮቴስታንታዊ የማላገጥና እንደ ፓስተር ዳዊት የሽሙጥ መንፈስን ተዋህደው የሰፈሩበት መናፍቅ ሲሆን ቅዱሳን አባቶችን ብቻ ሳይሆን ቅዱሳን መላእክት ላይ የተሳለቀ ሲሆን ይባስ ብሎ ።ምንም ክፉ አላደረግሁም ሲል አያፍርም።

    ReplyDelete
  9. Emigerm nwu!
    Betemesasy yenesu pasteur tesadbo kabeka behuala endihu mekadun enastawsalen.

    Egzabheir yemarachewu

    ReplyDelete
  10. ለሱ ብቻ ሳይሆን የስድብ መንፈስ ለተናወጣችው በሙሉ ልቦና ይስጣችው።

    ReplyDelete
  11. የኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤ/ክርስቶያን ጠላቶች ካሰለጠኑዋቸው ፕሮቴስታንታዊ ጂሀዲስቶች ውስጥ የለየለት የጥላቻና የማበሻቀጥ፣ የፅርፈት መንፈስ የተፀናወተው ለመሆኑ የመድረክ ትወናው በቂ ምስክር ነው።ይህ ሰው ራስ ቲያትር ይሰራ በነበረበት ጊዜ ውስጥ ቅዱስ ራጉኤል ቤተክርስቲያንን ሳይሳለም ስራ አይገባም ነበር።ሆኖም ሰው የፈለገውን እምነት መከተል ከፈጣሪው ተቸረው መብቱ ቢሆንም የሌላውን ያውም የነበረበትን አምነት በፀያፍና ፍፁም ኢግብረገባዊ በሆነ ትወና ልጆቹ የሚ ያፍሩበትን ቅርስ ማስተላለፍ እጅግ የዘቀጠ ተግበሰር ሲሆን ያሁኑ ምን አጥፍቼ ልፈፋ ደግሞ እጅግ አስቀያሚው ገፅታ ነው።ነገር ግን ባንድ በኩል ሳየው በትወናው ነውር ውስጡ ገብቶ ሲያስተወነው የነበረው እርኩስ መንፈስ ህሊናውን ተቆጣጥሮት እንደነበረ ነው ለማንኛውም አምላከ ቅዱሳን ፍርዱን ሳይውል ሳያድር ይስጥልን።የሚፀፀት ልቦና የለውምና!!!

    ReplyDelete
  12. U know what . በዚህ ሰው ለምን ትገረማላችሁ?? እርሱ እኔ እስከማውቀው ድረስ ከፌዝ እና ቧልት በስተቀር ድራማ መስራት መች ያውቃል? ለዚህ ነው መጽሐፍ ቅዱስ ፌዘኛ መሆንን የማይደግፈው። ሁሉም ሰው ሲስቅለት ያማረበት እየመሰለው በሁሉም ነገር ማሾፍ ይጀምራል። ይህን ደግሞ እነ አለልኝ መኳንንት ከሚሰሩት ድራማ ማየት ትችላላችሁ። አስተማሪነታቸውን ስነስርአታቸውን ።ስነጥበብ social value በጠበቀ መልኩ መተላለፍ እንዳለበት አምናለሁ። የእርሱ ድራማዎችስ? ምን ያስተምራሉ? የህን ለእናንተ እተወዋለሁ።

    ከሁሉ የገረመኝ ግን ይህን አይነት ይዘት ያለው ድራማ የሚያስተላልፉት የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እና ቲያትር ቤቶች ናቸው። ብሔራዊ value ሳይጠብቅ አንዱን የሚያንቋሽሽ ሌላውን የሚያሞግስ ነገር ይዘው አደባባይ የሚወጡት። ይቅርታ መጠየቅ ካለባቸው ይህን ፕሮግራም ያስተላለፈው አካል ነው። እርሱማ አንድ የራሱ የሆነ አስተሳሰብ ያለው ተራ ሰው ነው።

    ብቻ ለሁላችን ልቦና ይስጠን።

    ReplyDelete
  13. አይ እናንተ መናፍቃን ማለት እኮ እንደ ቀፎ የዲያብሎስ መስፈሪያ ናቸው። ስለዚህ መንፈሱ ያዘዛቸውን ሁሉ ቢያደርጉ የሚደንቅ አይሆንም። ለዚህም ስንኩል እግዚአብሔር ልብ ይስጠው። በእውነቱ ባለፈው ዓመት የትንሣኤ ዋዜማ ላይ በጾም ላይ ያላገጠው ማላገጥ ፣ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የጥምቀተ ባሕር እና የመስቀል አደባባዮች ላይ ጉባኤ እያዘጋጀ ትርምስ ሲፈጥር (በተለይ የጉደሩን መቸም አይረሳውም) ፣ በድራማው ላይ ከደበሽ ተመስገን እና ሌሎችም የክፋት ባልደረቦቹ ጋር ሆነው ቤተክርስቲያንን ሲሳደቡ ፣ ለተመለከተ የዛሬው ውሸቱ የሚያስተዛዝብ ይሆናል። "የስድምብ አፍ ተሰጠው ቅዱሳንንና ማደሪያውን ይሳደብ ዘንድ" የተባለው የአውሬው መንፈስ እንደሰፈረበት ምንም ጥርጥር የለውም። ከዚህ ቁራኝነት እንዲያድነው በጸሎት ማሰቡ መልካም ይመስለኛል። ወዶ አይመስለኝምና።

    ReplyDelete
  14. YELAW yaymero bekat yhe naw

    ReplyDelete
  15. ጥላሁን ጉግሳ ከዚህ በላይ ማሰብ እንደማይችል ማንም ይገባዋል፣ ነገር ግን ከ እንግድህ በግለሰብም ደረጃ ሆን ቤ/ክ በትእዝብት እንደማይታለፍ በእርግጠኝነት ልገባው ግድ ይላል !!

    ReplyDelete