Thursday, September 11, 2014

‹‹የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት በ2007 ዓ.ም ወደ ቀደመ ቦታው ይመለሳል››የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ፍቃደ ኃይሌ


(አንድ አድርገን መስከረም 01 2007 ዓ.ም)  ፡- ከሁለት ዓመት በፊት በቀላል ባቡር ግንባታ ምክንያት ከቦታው ተነስቶ የነበረው የአቡነ  ጴጥሮስ ሐውልት በአዲሱ ዓመት 2007 ዓ.ም በእርግጠኝነት  ወደ ቦታው እንደሚመለስ የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ፍቃደ ኃይሌ ተናገሩ፡፡ ከቀናት በፊት በወርሀ ጳግሜ የ2006 ዓ.ም ስራ አፈጻጸምን በሚመለከት እና የ2007ዓ.ም  ስራ ተግባራትን በሚመለከት በጽሕፈት ቤታቸው ለጋዜጠኞች ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡ የተቋሙ ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ፍቃደ ኃይሌ የአቡነ ጴጥሮ ሐውልት ቀድሞ ከነበረበት ቦታ ላይ በአዲሱ አመት እንደሚመለስ ተናረዋል፡፡

ቦታው የባቡር መመላለሻ እንደመሆኑ መጠን ከበታች ለሚነሳው የመሬቴ ንቅናቄ በሀውልቱ ላይ ለሚያደርሰው አደጋ በሚመለከት ለስራ አስኪያጁ ለተነሳላቸው ጥያቁ በሰጡት ምላሽ ‹‹ ሐውልቱ በሚመለስበት ጊዜ በባቡሩ ምክንያት ለሚከሰተው ንቅናቄ(Vibration) በሐውልቱ ላይ ለሚያደርሰው አደጋ በሚመለከት በባለሙያዎች ተጠንቶ ሐውልቱ በቀደመ በቦታ ላይ የሚቀመጥ መሆኑን›› ስራ አስኪያጁ  ጠቁመዋል፡፡  

ይህ ሐውልት ቀድሞ ከቦታው ላይ በተነሳበት ወቅት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ቤተ ክህነት እንደማንኛው ዜጋ የመነሳት ዜናው ከመገናኛ ብዙሐን መስማቱ ይታወሳል ፤ ሆኖም ሐውልቱ በሚነሳበት ወቅት ተቋሙ ጥሪ ተደርጎለት የሐውልቱን ክብር በሚጠብቅ መልኩ ከነበረበት ቦታ ወደ አምስት ኪሎ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም መሸኝቱ ይታወቃል፡፡
ሐውልቱ በሚነሳበት ወቅት

……. ሐውልቱ  ወደ ቦታው በሚመለስበት ወቅት ቤተክህነቱ ቤተ ክርስቲያኒቱን በመወከል ለሐውልቱ መደረግ ያለበትን ጥንቃቄ ከሚመለከታቸው ባለሙያዎች ጋር በመነጋገር ቀድሞ የነበረበት ቦታ ላይ የማስመስ ግዴታ እና ኃላፊነት ያለበት መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡
 መልካም አዲስ ዓመት

1 comment: