Tuesday, December 23, 2014

እነሆ ቤተ ክርስቲያን ዛሬ ደስ አላት





አንድ አድርገን ታኅሳስ 15 2007 ዓ.ም


የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕክምና ትምህርት ክፍል የተቋቋመው የዛሬ 50 ዓመት በ1957 ዓ.ም በስድስት ተማሪዎች ብቻ ነበር፡፡ ዛሬ ከአምስት አስርት ዓመታት በኋላ በታሪኩ ከፍተኛ የሆኑት 287 ሐኪሞችን ባሳለፍነው ሳምንት ታኅሳስ 12 2007 ዓ.ም 50ኛ ዓመቱን በሚያከብርበት ልዩ ጊዜ ማስመረቅ ችሏል፡፡ ከተመረቁት ተማሪዎች መካከል ከ140 ተማሪዎች በላይ የማእረግ ተመራቂዎች ነበሩ፡፡ እነሆ በዚህ ዓመት ከተመረቁት ከ100 በላይ ሐኪሞች በስርዓተ ቤተ ክርስቲያን በግቢ ጉባኤ ታቅፈው ትምህርታቸውን ከእምነታቸው አንድ በማድረግ ቀን በትምህርት ለሊት በአገልግሎትና በስራ ላለፉት ስድስት እና ሰባት ዓመታትን በርካታ ውጣውረዶች ካሳለፉ በኋላ የዘመናት ህልማቸውን እንደ እግዚአብሔር መልካም ፍቃድ ሊያዩ ችለዋል፡፡

እነሆ ቤተ ክርስቲያን ዛሬ ደስ አላት የሚተጉ፣ የሚጸልዩ፣ የሚቀድሱ ፤ የሚያስቀድሱ፣ እግዚአብሔር ይማርህ የሚሉ፣ የሚጾሙ፣ የሚዘምሩ፣ የሚያስተምሩ፣ የሚማሩ፣ ‹ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ› የሚሉ፣ የሚላኩ፣ የሚታዘዙ ፤ የሰዎችን ችግር የሚፈቱ በርካታ ሐኪሞችን አገኘች፡፡ በጥቁር አንበሳ ግቢ ጉባኤ ታሪክ በመንፈሳዊ ትምህርትም የጸኑ እንደዚህ ብዙ ተመራቂ ሐኪሞችን ታይቶ አይታወቅም፡፡ ከዘንድሮው ተመራቂ ሐኪሞች መሐል 32/ወይም ከዚያ በላይ/ ወረብ አቅራቢ ተመራቂዎች ነበሩ፡፡ ይህን ያህል ወረብ አቅራቢ ይቅርና ተመራቂ እንኳን ማግኘት በቀደሙት ዓመታት አስቸጋሪ ነበር፡፡ በግቢ ጉባኤ በመንፈሳዊ ትምህርትም ጸንተው በመስቀልና በመጽሔት የተመረቁ ደግሞ 80 በላይ ሐኪሞች ናቸው፡፡

እግዚአብሔር ይባርካችሁ ፤ የአገልግሎት ዘመናችሁን ይባርክላችሁ ፤ 

እንኳን ደስ አላችሁ፡፡



10 comments:

  1. ደስታው ለሁላችንም ነው፡፡እኔም የእናንተን ጥዑም ቃል ልደገመውና ቤተክርስቲያን እንኳን ደስ አለሽ ልበል፡፡እንዲህ ዩኒቨርሲቲዎችን እያሰፋና እያስፋፋ ምሁራንን በማብዛት ቀጥተኛ ያልሆነ እርዳታ የሚያደርግልን የኢሀአዴግ መንግሥትም ምስጋና ይገባዋል፡፡አሁንም እግዚአብሔር የጠመመውን እንዲያቀና፣ጥራት የጎደለውን ጥራቱን እንዲያስጠብቅ ማስተዋሉን ያድለው፡፡
    ውድ ኦርቶዶክሳዊ ተመራቂዎች የአባቶቻችሁን ሥርዓትና የቤተክርስቲያንን ሕግ አክብሮ አስከብሮ ለመኖር ያብቃችሁ፡፡በሙያችሁ ለማገልገል አምላክ ይርዳችሁ፡፡ደስ ብሎናል፡፡

    ReplyDelete
  2. ደስ ይበለን በጣም

    ReplyDelete
  3. amlake esrael yebezan

    ReplyDelete
  4. እግዚአብሔር ይባርካችሁ ፤ የአገልግሎት ዘመናችሁን ይባርክላችሁ ፤

    እንኳን ደስ አላችሁ፡፡

    ReplyDelete
  5. ውድ ኦርቶዶክሳዊ ተመራቂዎች የአባቶቻችሁን ሥርዓትና የቤተክርስቲያንን ሕግ አክብሮ አስከብሮ ለመኖር ያብቃችሁ፡፡በሙያችሁ ለማገልገል አምላክ ይርዳችሁ፡፡ደስ ብሎናል፡፡

    ReplyDelete
  6. wow betam betam betam 10000000000000000000 times እነሆ ቤተ ክርስቲያን ዛሬ ደስ አላት we are very very very happy happy who lives over seas by your achieving such a marvelous result and success and May GOD bless you all. DINGLE titebekachu kefit timirachu kehula Tiketelachu, Kidus MICHAEL be Kinfe Redeetu yetebekachu, EGZIABHERE yasenachu. BERTU

    ReplyDelete
  7. እውነት ውጠን ነዘረኝ ደስ ሰሲል ቤተክርስቲያን እንኳን ደስ አለሽ

    ReplyDelete
  8. ደስታው ለሁላችንም ነው፡፡እኔም የእናንተን ጥዑም ቃል ልደገመውና ቤተክርስቲያን እንኳን ደስ አለሽ ልበል፡፡እንዲህ ዩኒቨርሲቲዎችን እያሰፋና እያስፋፋ ምሁራንን በማብዛት አሁንም እግዚአብሔር የጠመመውን እንዲያቀና፣ጥራት የጎደለውን ጥራቱን እንዲያስጠብቅ ማስተዋሉን ያድለው፡፡
    ውድ ኦርቶዶክሳዊ ተመራቂዎች የአባቶቻችሁን ሥርዓትና የቤተክርስቲያንን ሕግ አክብሮ አስከብሮ ለመኖር ያብቃችሁ፡፡በሙያችሁ ለማገልገል አምላክ ይርዳችሁ፡፡ደስ ብሎናል፡፡

    ReplyDelete
  9. Egzeabhere Yemesgen!!! I am proud of you. We need more of you.

    ReplyDelete
  10. Yes, fitsum des yilal!!!! Dear, graduates of the church, bertuuuuuuuuuuuuuuu!!!!! Yenefs Dr. Engineer, Dn., Papas, etc yelatiminna endelijinetachu hulem bertu!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

    Tesfalegn Ze Debre Eba!!!!!

    ReplyDelete