Saturday, February 21, 2015

እንዲህ ነው መከተል! ክርስቶስን መምሰል!


ጳውሎስስ ምን አለ......

እኔ ክርስቶስን እንደመሰልሁ ሁሉ
እናንተም እንዲሁ እኔኑ ምሰሉ

አመንሁ በሚል ብቻ ጌታን ላለመምሰል
ሊቀበል ታገሰ እጅግ ብዙ በደል
በዚህም ጌታውን አብልጦ ወደደ
ሞቱንም ለመቅመስ እንደበግ ታረደ

ጌታን ፍጹም ወዶ ሁሉን ነገር ጥሎ
የኖረው ለወንጌል እርሱን ተከትሎ
በመጨረሻውም አምላኩን መሰለ
ለጌታ ክብር ሲል ቁልቁል ተሰቀለ


እናም ወዳጆቼ

በክርስቶስ መኖር ምርጫችሁ ከሆነ
ከዚህ ጠማማ ዓለም ዓይኑን ከጨፈነ
በሥጋ እየሄደ በቁም ከበደነ
ምን ጉዳይ አላችሁ ይልቅ ተከተሉት
በቃል ብቻ ሳይሆን በግብርም ምሰሉት
የኢየሱስ ተከታይ ክርስቲያን ነኝ የሚል
ታርዶ ሲሞት እንጂ አይታይም ሲገል፡፡
ይሄው ነው እንግዲህ የክስቲያን ውርሱ
እጅግ የመረረ ሞት ጽዋን መቅመሱ፡፡


…………መላኩ … 15-06-07......

1 comment: