Friday, April 10, 2015

አቶ አሸናፊ የጻፋቸው ኦርቶዶክሳዊ ያልሆኑ ትምህርቶች ከቤተክርስቲያ ደጃፍና ከምዕመናን እጅ የሚወገዱበት መንገድ ያሳስበናል




አንድ አድርገን ሚያዚያ 01 2007 ዓ.ም

ከሦስት ዓመት በፊት ግንቦት የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ላይ አንድ ወሳኝ ውሳኔ መወሰኑን ይታወቃል ፤ በውሳኔውም በርካቶች ከቤተክርስቲያን ጋር የጀርባ ቅማል ሆነው ምንፍቅናቸውን ሲዘሩ የነበሩ ሰዎች በግልጽ ጉባኤ የተወገዙበት ቀሪዎቹ ደግሞ መዝገባቸው በይደር የቆየበት እንደሆነ የምናስታውሰው ነው፡፡ በጊዜው  በፕሮቴስታንቶች እየተደገፉ የቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ትምህርተ ሃይማኖት፣ ሥርዐተ እምነት፣ ክርስቲያናዊ ትውፊትና ታሪክ በኅቡእና በገሃድ ተደራጅተው ለማፍረስና ለማፋለስ እየተንቀሳቀሱ  ድርጅቶች ፍጹም ውግዘት የሚገባቸውን የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ እንቅስቃሴ አራማጅ ማኅበራትና ግለሰቦች በመለየት ማኅበረ ሰላማ፣ ማኅበረ በኵር፣ የምሥራች አገልግሎት፣ አንቀጸ ብርሃን፣ የቅድስት ልደታ ለማርያም መንፈሳዊ ማኅበር፣ የኢትዮጵያ መንፈሳዊ ተሐድሶ ኅብረት፣ አሸናፊ መኰንን፣ አግዛቸው ተፈራ፣ ጽጌ ስጦታው እና ግርማ በቀለ የመሰሉት ሰዎችና ላያቸው ማር የተቀቡ ውስጣቸው ግን ነጣቂ የሆኑ ተቋማት ተለይተው መለየታቸው ይታወቃል፡፡






አቶ አሸናፊ በንስሃ ታጥቦ ወደ ቅድስት ቤተክርስቲያን ከመመለስ ይልቅ  ቅዱስ አትናቴዎስ የወንጌል አገልግሎት በማለት  ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን በምታከብራቸው  የእምነቷ አካል አድርጋ በምትዘክራቸው በቅዱስና በጻድቅ ሥም ሌላ የእምነት ተቋም  ከመሰሎቹ ጋር በታህሳስ 2006 .  ማቋቋሙ ይታወቃል፡፡ ይህ ሰው ከቤተክርስቲያን በአባቶች ሳይለይ በፊት የጻፋቸው መጽፍች ግን አሁንም ድረስ ለየዋሃን ምዕመናን ገንዘባቸውን ብቻ በሚያሳድዱ የመጽፍት ሻጮች አማካኝነት በየቤተ ክርስቲያኑ ደጃፍ እየተሸጡ ይገኛሉ፡፡  እኛ አሁን ላይ ግድ የሚለን የዚህ ሰው መጽፍቶች በምዕመኑ ላይ የሚያሳድሩት ተጽህኖ እና ከኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ደጃፎች ላይ የሚወገዱባቸው አግባብ ነው፡፡ አቶ አሸናፊ ከቤተክርስቲያን ሳይለይ በፊት እጅጉን የተመከረ ሰው ነበር ልቡ አንድ ጊዜ ስለደነደነ መስማትን ፍቃድ አላደረገም ነበር ስለዚህ ተመክሮ አልሰማ ያለን ሰው ከቤተክርስቲያን በቅዱስ ሲኖዶስ ተገሎ የራሱን የእምነት ተቋም ስላቋቋመ ሰው ግድ የሚለን እኛ ማነን?  ቅድሚያ  አቶ አሸናፊ  የጻፋቸው  ኦርቶዶክሳዊ ያልሆኑ ትምህርቶች ከቤተክርስቲያ ደጃፍና ከምዕመናን እጅ የሚወገዱበትመንገድ ቢያሳስበን መልካም ነው፡፡  መጽሐፍት ላነበባቸው መንገድ የማሳየት አቅማቸው ከፍተኛ ስለሆነ በመጀመሪያ በሰውየው የተጻፉ 30 በላይ የምንፍቅና መጻሕፍት  እና መሰል ፅሑፎች አወጋገዳቸው ሊያስጨንቀን ይገባል  

 
ቅዱስ ሲኖዶስ እነዚህን ግለሰቦች በቅዱስ ሲኖዶስ የተወገዙ መሆናቸው ታውቆ በነበረው የካህንና የክብር ስም እንዳይጠሩና በቤተክርስቲያን በማናቸውም መድረክ ላይ እንዳይሳተፉ ›› ብሎ ቢወስንም ይህ ሰው ቅዱስ ሲኖዶስ አውግዞ እና ሕፀጽ አለበት ካለ በኋለ ስለምንዲያቆንእየተባለ ይጠራል?



በጊዜው የተወገዙት ሰባቱ  ድርጅቶች ውስጥ  ከሣቴ ብርሃን ፤ ማኅበረ ሰላማ ፤  የምሥራች አገልግሎት ፤ የቅድስት ልደታ ለማርያም መንፈሳዊ ማኅበር ፤  አንቀጸ ብርሃን (ከድርጅቱ ጋራ አሸናፊ መኰንንና ዳንኤል ተሾመ) ፤ የእውነት ቃል አገልግሎት ፤ ማኅበር በኵርና የኢትዮጵያ መንፈሳዊ ተሐድሶ ኅብረት ይገኙበታል ፡፡ ከእነዚህ በተጨማሪ ከተወገዙት 16 ሰዎች  የክህነትና የክብር ማዕርጋቸው ተሽሮ የበፊቱ አቶ የሚለው ስም ከተመለሰላቸው ውስጥ በግንባር ቀደምነት  አቶ አሸናፊ መኰንን ይገኝበታል፡፡


ይህ ሰው ለዘመናት ኦርቶዶክሳዊ በመምሰል የእኛ ያልሆነ ትምህርት ኑፋቄ የተቀላቀለበት መጽሃፍቶችን በመጻፍ በርካታ ብሮችን መሰብሰብ ከመቻሉም በተጨማሪ ምንፍቅናውን በበርካታ መጽሃፍቶች መዝራት ችሏል ፤ አሁን ግን ይህ ሰው ስራው ታውቆበት ከቤተክርስትያን ከተባረረም በኋላ የመጽሀፍት ነጋዴዎች በማወቅም ይሁን ባለማወቅ መጽሀፍቶቹ ከትክክለኛ መጽሀፍቶች ጋር በመደባለቅ በገበያ ላይ ይዘዋቸው  ይገኛሉ ፤ ስለዚህ ምዕመናን የዚህን ሰው ትምህርት እና መንገድ ቤተክርስትያን ስላወገዘች መጽሀፍቶቹን እና ትምህርቱን በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ከመጠቀም ወደ ኋላ እንዲሉ “አንድ አድርገን” መልዕክቷን ታስተላልፋለች፡፡ ለዚህም ማስረጃ ይሆን ዘንድ መጽሀፎቹን ላያቸው ተዋህዶ ፤ ውስጣቸው ተሐድሶ የሆኑ መጻህፍት የፊት ሽፋን በመውሰድ በቀላሉ መለየት እንድትችሉ በዚህ መልክ አቅርበንላችኋል፡፡ 

”የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ በውሥጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኵላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ።” የማቴዎስ ወንጌል 7፤15







15 comments:

  1. አንድ አድርገኖች ጥያቄ አለኝ???

    1) በአስቆረቱ ይሁዳ ሐጢአት ሌሎች ሐዋርያት ተጠይቀው ነበርን?
    2) በንስሐ መመለስ የሚባል ነገር የለም?
    3) አንዳንድ መነኩሲዎች በዝሙት በመውደቃቸው ምክንያት ኦርቶዶክስ መወገዙዋ ትክክል ነውን?
    4) ማን የስህተት አስተማሪ እንደሆነስ ተጠቃሚው ሕዝብ ምንም አያውቅም ማለት ነውን?
    5) እውነተኛ ክርስቲያኖችን ወይም ሰባኪዎችን እንዴት እንወቃቸው?
    6) ክርስትና ፍቅር ሆኖ ሳለ በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ግን በተቃራኒው ጥላቻ፣ ክፋትና መነቃቀፍ ከየት መጣ?
    7) በአጠቃላይ በዚች ታሪካዊ ቤት ክርስቲያናችን ላለው መነታረክና መበጣበጥ (በውስጥም በውጪም አገር) መፍትሔው ምንድነው? ብላችሁ ታስባላችሁ? በዚህ ላይስ በርትቶ መስራት አይሻልምን?


    ለበቤተ ክርስቲያናችን ምህረት ከእግዚብሔር ብቻ ይምጣልን!!!!

    መፍትሔ! መፍትሔ!! መፍትሔ!!!

    ሰላም ይብዛላችሁ!!!
    አክባሪ ወንድማችሁ

    ተናገር ነኝ


    ReplyDelete
    Replies
    1. ሄይ ያልከው ሁሉ ሞኝነት ነው እባክህ የተነሳ ቢነሳ ወቅቱ ነው የሚሻለው ግን በሚወሰደው መፍትሄ አድርግ አሰተያየት ሰጪው

      Delete
  2. WHY YOU DON'T WANT TO POST MY 7 QUESTIONS? LET YOU KNOW THAT IT IS NOT ONLY MINE, BUT WE ARE ABOUT 12 MAHEBERTEGNOCH JUST TO GET CONFIRMATION WHETHER YOUR ARE DOING A FAIR JOB OR NOT FOR OUR MAIN CHURCH THESE QUESTIONS HAVE BEEN SENT TO YOU!!!

    GOD BLESS YOU,

    TENAGER

    ReplyDelete
  3. እኔ እንደሚመስለኝ ቤተክርሰቲያን መጀመሪያ የሰጠችውን ማዕረግ ስለገፈፈችው። እሱ በአንቢታ ማዕረጉን መጠቀሙን ስላላቆመ ከሳ ስሙን እንዳይጠቀም ማድረግ ይኖርባታል። ያው አቶ እንደሆነው አቶ እያለ ይቀጥል። በዋነኛነት ምዕመናንን የሚያሳስታቸው ዲያቆን የሚለው ስም መጽሐፉ ላይ መኖሩ ነው። ስለዚህ ቤተክርሰቲያን ስምዋን የምታስመልስበት ሥራ ላይ ትኩረት ቢደረግ መልካም ይመስለኛል። እሱን ማድረግ ከተቻለ ሌላው ነገር ቀላል ነው።

    ReplyDelete
  4. ምነው ስለ ግብረ ሰዶምም ትንሽ ብትሉ ምናለ ? ይህ ትውልድ የሚገድል ክፉ መንፉስ ነው

    ReplyDelete
  5. ምነው ስለ ግብረ ሰዶምም ትንሽ ብትሉ ምናለ ? ይህ ትውልድ የሚገድል ክፉ መንፉስ ነው

    ReplyDelete
  6. I have been read your books and news paper for such long time ,could not change my life it does not even talk about jesus and gospel. You guys are not trying to preach gospel but only trying to keep traditions . For more than a decade you have been a cancer of our orthodox church you pushed out dozens of preacher from our charge what you did you gain from that? As a result of of wrong principle our chrch are shrinking by number and size from time to time you rather taking out of people instead of giving advice and join him to church.On contrary I have read a bout 10 books of DIAKON ashenafi mekonen and heard almost all his preaching, all talks a bout jesus and really touches my heat i could not find any wrong teaching as what you accused him,I think you guys don't like for those who preach jesus deeply. To be clear we will continue to read DIAKONE ashenafi books and will listen his preaching too. Farewell mahber kedusan.

    ReplyDelete
  7. I really like Deacon Ashenafi Preaches. I don't care you call him Ato or Deacon. I evaluate people based on their message. I don't know this guy personally, but I found him on YouTube. May God gives his wisdom again and again. People who rush to judge people make me sick.

    ReplyDelete
    Replies
    1. that is my point . may jesus our lord be with you

      Delete
  8. Calling him Deacon or Ato doesn't make a difference on his identity, but the the preaches he has made has a big difference on his listeners. I am his witness. May be the people who sell his book might know he is the best writer. The merchant know whose book sell easily. Believe it or not I have ordered his book

    ReplyDelete
  9. እስቲ ዝም በሉ መጀመሪያ ቤተክርስቲያን ባለቤት ታግኝ ያኔ ሁሉም ይሆናል፡፡ እነዚህ ሕፀፅ ስለተገኘባቸው ስዎች የሚፅፉትም ሰዎች እኔ ብዙ አያስደስቱኝም፤ ምክንያቱም ስዎች ምን ይላሉ ለማለት ያሕል የሚፅፉ ይስለኛል ፡፡ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ቤተክርስቲያን እውነተኛ ጠባቂና እረኛ እውነተኛ አማኝ ይኖራታል አይቀርም ዝም ብለን እንፀልይ ምክንያቱም እሰካሁን ባለው አካሄድ አንዱ አንዱን መክሰስ ስለተከሳሹ እጅግ ብዙ ማለትና ማድረግ እየተቻለ ቁንፅል ነገር ቆንጥሮ ማሳየት የትም አላደረሰም፤፤ ማንም በጀመረው መንገድ ሲገፋበት አልታየም ይጀመራል ይቀራል፡፡ውስጥ አዋቂ ነን እያላችሁ ግን አንዱን ተንኮስ ሌላውን ድፍንፍን ማድረግ ከነዚ ግልጽ ከወጡት ታሃድሶዎችና መነፍቃን ተለይቶ መታየት አደለም የባሰ እንደዉም በደል ነው ፡፡ በመጀመሪ ደረጃ የዚህ ፅሁፍ ፀሃፊ ስም ድብቅ ነው አለተገለፀም ሲቀጥል ይህ ማሳሰቢያ ለማነው ጥያቄውስ ለማን ለኛ ለምእምን ከሆነ እኛ ራሳችንን ማፅናት የእግዚአብሔር ቀን እሰኪመጣ መፀለይ እንጂ አንመካም በጉልበታችን ፤ ቤተክርስቲያን ውስጥ ላሉት ጉልበተኞች ከሆነ አድራሻውን በትትክል መፃፍ ለ------ ተብሎ እሺ!!! ከዚህ በተረፈ ቤተክርስቲያናችን በዚህ ዘመን ሃብቶቿ ውስጧ የተሰገሰጉት በመስቀልና በቆብ ያሸበረቁት፣ በማስመሰል አለንልሽ የሚሉ አቋማቸው ግልፅ ያልሆነ ወላዋይ ፈሪሳውያን ሳይሆኑ፤ ምንም የማያውቁት በንጹህ ልቦና የሚመላለሱት ምዕመናኖቿ ብቻ ናቸው እሰከ ቀኗ ድረስ፡፡ስለዚህ የቤተክርስቲያን ነገር ያገባኛል ከሆነ እየተባለ ያለው ቆራጥነትን ይጠይቃል አለበለዚያ አገም ጠቀሙን ተወው፡፡ እኛም አውቀናል ጉድጓድ ምሰናል ይባል የለ!!!

    ReplyDelete
  10. እስቲ ዝም በሉ መጀመሪያ ቤተክርስቲያን ባለቤት ታግኝ ያኔ ሁሉም ይሆናል፡፡ እነዚህ ሕፀፅ ስለተገኘባቸው ስዎች የሚፅፉትም ሰዎች እኔ ብዙ አያስደስቱኝም፤ ምክንያቱም ስዎች ምን ይላሉ ለማለት ያሕል የሚፅፉ ይስለኛል ፡፡ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ቤተክርስቲያን እውነተኛ ጠባቂና እረኛ እውነተኛ አማኝ ይኖራታል አይቀርም ዝም ብለን እንፀልይ ምክንያቱም እሰካሁን ባለው አካሄድ አንዱ አንዱን መክሰስ ስለተከሳሹ እጅግ ብዙ ማለትና ማድረግ እየተቻለ ቁንፅል ነገር ቆንጥሮ ማሳየት የትም አላደረሰም፤፤ ማንም በጀመረው መንገድ ሲገፋበት አልታየም ይጀመራል ይቀራል፡፡ውስጥ አዋቂ ነን እያላችሁ ግን አንዱን ተንኮስ ሌላውን ድፍንፍን ማድረግ ከነዚ ግልጽ ከወጡት ታሃድሶዎችና መነፍቃን ተለይቶ መታየት አደለም የባሰ እንደዉም በደል ነው ፡፡ በመጀመሪ ደረጃ የዚህ ፅሁፍ ፀሃፊ ስም ድብቅ ነው አለተገለፀም ሲቀጥል ይህ ማሳሰቢያ ለማነው ጥያቄውስ ለማን ለኛ ለምእምን ከሆነ እኛ ራሳችንን ማፅናት የእግዚአብሔር ቀን እሰኪመጣ መፀለይ እንጂ አንመካም በጉልበታችን ፤ ቤተክርስቲያን ውስጥ ላሉት ጉልበተኞች ከሆነ አድራሻውን በትትክል መፃፍ ለ------ ተብሎ እሺ!!! ከዚህ በተረፈ ቤተክርስቲያናችን በዚህ ዘመን ሃብቶቿ ውስጧ የተሰገሰጉት በመስቀልና በቆብ ያሸበረቁት፣ በማስመሰል አለንልሽ የሚሉ አቋማቸው ግልፅ ያልሆነ ወላዋይ ፈሪሳውያን ሳይሆኑ፤ ምንም የማያውቁት በንጹህ ልቦና የሚመላለሱት ምዕመናኖቿ ብቻ ናቸው እሰከ ቀኗ ድረስ፡፡ስለዚህ የቤተክርስቲያን ነገር ያገባኛል ከሆነ እየተባለ ያለው ቆራጥነትን ይጠይቃል አለበለዚያ አገም ጠቀሙን ተወው፡፡ እኛም አውቀናል ጉድጓድ ምሰናል ይባል የለ!!!

    ReplyDelete
  11. እኔ አብዛኛን መፅሀፍቶቸቹን አንብቤአለሁ፡፡ ምኑ ጋር ነው ህፀፁ፡፡ ከናንተ የይልቅ የሊቃውት ጉባዔን ዝርዝር መግለጫ ማንበብ ብንችል ሚዛናዊ እንሆናለን፡፡

    ReplyDelete