Thursday, November 5, 2015

“ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቷል”

በጥበቡ በለጠ
(አንድ አድርገን ጥቅምት 20 2006 ዓ.ም) ከሰሞኑ የሐገራችን አጀንዳ ሆነው የከረሙት መምህር ግርማ ወንድሙ ናቸው። በተለያዩ ድረ-ገፆች እና የፌስ ቡክ ተጠቃሚዎች ዘንድ ስለ መታሠራቸውና ስለ መከሠሣቸው ጉዳይ የተለያዩ ፅሁፎች አስተያየቶች አቋሞች ሁሉ ሲንፀባረቁ ቆይተዋል። በርግጥ ጉዳዩ በፍርድ ቤት የተያዘ ስለሆነ ምንም ማለት ባይቻልም ስለ ኢትዮጵያ ሀገራችን የሀይማኖት እና የአማኝነት ጉዳይ እስኪ እንጨዋወት።

እኛ ኢትዮጵያዊያን ራሣችንን መጠየቅ ከራሣችን ጋር መነጋገር የሚገቡን በርካታ ጉዳዮች አሉ። ለምንድን ነው አንድን ጉዳይ በጭፍን የምንወደው ወይም የምንጠላው? ቲፎዞ ወይም ደጋፊ ካለው ነገር ጋር ወዲያው ተለጣፊ የምንሆንበት ክስተቶችን መናገርም ይቻላል። ከዚህ በፊት በ1980ዎቹ አጋማሽ ላይ ባሕታዊ ገ/መስቀል የተባሉ ሰው ተነስተው ነበር። እኚህ ሰው አጥማቂ ናቸው። ወንጌል ሰባኪ ናቸው። የኢትዮጵያን መፃኢ እድል ተንባይ ወይም ነብይ ሁሉ ሆነው ብቅ አሉ። ብዙ ሺ ሕዝብ ተከታያቸው ሆነ። እርሣቸውም አንዴ አሜሪካ፤ አንድ ጊዜ እስራኤል ሌላ ጊዜ አውሮፓ ሌላ ጊዜ ደግሞ ገዳም ናቸው እየተባለ የሐገሪቱ ዋነኛው የመነጋገሪያ አጀንዳ ሆኑ።


“በዘንግ የሚገዛ መሪ ይመጣል ኢትዮጵያ ማርና ወተት የሚዘንብባት የተባረከች ሀገረ ትሆናለች። ከወደ ምስራቅ የተቀባው መሪ ይመጣል፤” ወዘተ የሚሉት - የባሕታዊ ገ/መስቀል ደማቅ ንግግሮች ነበሩ፤ መጨረሻ ላይ ግን በአፀያፊ ድርጊቶች ተከሰው ለእስራት ተዳረጉ። ከዚህ ጦስ ጋር በተያያዘ ብዙዎች ተጐዱ:: በእርሣቸው መልዕክተኝነት እና ተአምር ሰሪነት ያመኑ ሰዎች ተፈውሰናል ያሉ ሰዎች በመንፈስ መጐዳታቸው አይቀርም። አምነውባቸዋልና ነው።

በዚሁ በ1980ዎቹ አጋማሽ ላይ ሌላ ባሕታዊም ዝነኛ ሆነው ብቅ አሉ። አባ አምሃስላሴ ይባላሉ። እርሣቸውም በሺዎች ተከበውና ታጅበው የሚንቀሣቀሱ ነበሩ። የኢትዮጵያን መፃኢ እድልም ይናገሩ ነበር። በኋላ ላይ በእርሣቸው ፊት አውራሪነት በአራት ኪሎ ቅድስተ ማርያም ቤተ-ክርስትያን ውስጥ እመቤታችን ተገለፀች፤ ታየች፤ ተብሎ የተፈጠረው ሁከት ግርግር ጩኸት ደስታ መከራ ምን ግዜም የማልረሣው ጉዳይ ነበር። እኚሁ አባት በኋላ ወደ ጐንደር አቅንተው ጐንደር ከተማ ላይ የተከሰተው ደም የመፋሰስ ድርጊት ሁሉ ተፈፅሟል።

ወደ ኋላ ዞር ብለን እነዚህን ድርጊቶች ክስተቶችን ስናስተውል ጭፍን ተከታይ በመሆናችን የመጡብን ጣጣዎች ናቸው። በርግጥ ለጭፍን ተከታይነታችን የሚያጋልጡን አያሌ ጉዳዮች አሉ። ዋናው ድህነታችን ነው። ድህነት ሰፊ ሀሳብ ነው፤ በተለይ ኢትዮጵያ ውስጥ ሲሆን ብዙ ትንታኔና ማብራሪያ ያስፈልገዋል። በዓለም አደባባይ ላይ በረሃብ እና በድርቅ የምትጠራ ሐገር ውስጥ ተወልደን ያደግን ዜጐች ነን። መሠረታዊ የሚባሉ የሰው ልጅ ፍላጐቶች ገና ምኑም ያልተሟሉባት ሀገር ልጆች ነን። የአለም ስልጣኔና ግስጋሴ ጥሎን ሔዶ እኛ ገና ከአነስተኛና ጥቃቅን ነገሮች እንጀምር ብለን ልማት ውስጥ የገባን ነን። ግብርናችን ዛሬም፤ የዛሬም ሦስት ሺ አመት ተመሣሣይ ነው። 85 በመቶ ሕዝባችን በገጠር የሚኖር ነው። ገጠር ማለት ደግሞ ከብዙ ነገሮች የታቀበ ነው። መሠረታዊ የሕክምና አገልግሎቶች ያልተሟሉላት ሐገር ናት። ከበሽታው የሚፈውሰው ሃይል ያጣ ህዝብ ነው። ታዲያ እኛ ውስጥ ትንሽ ተአምራት የሚመስል ነገር ይዞ የሚመጣ ባህታዊም በሉት አዋቂ ልዩ ፍጡራችን ነው። ምክንያቱም እኛ ልንመልሣቸው ያልቻልናቸውን ጥያቄዎች እሱ ያወጋልናል፤ እሱ ይነግረናል፤ እሱ ተአምራት ሲሠራባቸው ያሣየናል። ስለዚህ እንከተለዋለን። ካለሱስ አዋቂ ማን አለ እንለዋለን። 

 ኢትዮጵያ ውስጥ የፈረንጅ አጥማቂዎችና ፈዋሾች ሳይቀሩ እየመጡ ነው። እዚሁ አዲስ አበባ ስታዲየም ውስጥ የፈውስ ኘሮግራም ተብሎ “ፈረንጆች ክራንች እያስጣሉ ነው። ከደዌ ከሰይጣን እያላቀቁ” ነው ተብሎ ትልቅ መርሃ ግብር ተደርጓል። በተለይ በደቡብ ኢትዮጵያ አካባቢ ደግሞ የፈረንጅ ፈዋሾች በተደጋጋሚ እየመጡ ብዙ ሺ ተከታይም ሲያገኙ አይተናል። የራሱን ሀገር ያልፈወሰ ኢትዮጵያ ወጥቶ ፈዋሽ ተብሏል። ይህ ሁሉ ጉዳይ ከየት መጣ ስንል የሚጫወትብን አንድ ጉዳይ አለ። ይህም አለማወቃችን ነው። እውቀት ጠፍቶብናል። መጽሐፍ ቅዱስ ትንቢተ ሆሴዕ ምዕራፍ አራት ቁጥር ስድስት እንዲህ ይላል “ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቶአል”

አዋቂ ሰው ይጠይቃል። አንባቢ ይጠይቃል። ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ አጥማቂ ነን፤ ፈዋሽ ነን የሚሉ ሰዎች ክብርና ዝናቸው ከፈጣሪ በላይ እየሆነ ነው። ማንበብ ያቆምን ስለሆነ አንጠይቅም:: አንድ ሰው ኢትዮጵያ ላይ እየተነሣ አንድ የሆነ ነገር ሲያሣየን ተነስተን ተከትለነው የምንጠፋው ለምንድን ነው? ምናልባት መጽሐፍ ቅዱሱን ራሱ በስርዓት ባለማንበባችን ባለማወቃችን ነው። ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቶአል የተባለውም ለዚህ ነው።

አሁን በቅርቡ እንኳን ኘሮፌሰር ነኝ፤ ዶክተር ነኝ ኢንጂነር ነኝ፤ ፓይለትም ልሆን ነው እያለ ሲያስተምረን የነበረው ሣሙኤል ዘሚካኤልን ማስታወስ ብቻ ይበቃናል። ሣሙኤል ዘሚካኤል የዋሸው ተራውን ሕዝብ አይደለም። ዩኒቨርሲቲዎችን እና ጠቢባን ናቸው ተብለው የተቀመጡትን ኢትዮጵያዊያንን ነው። በ27 ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እየተዘዋወረ የማነቃቂያ ንግግር ያደርጋል። ባራክ ኦባማ የቅርብ አለቃዬ ነው፤ ፑቲን ጓደኛዬ ነው፤ ማንዴላ ቤት በተደጋጋሚ ሔጄ ስለ ኢትዮጵያ ተጨዋውተናል፤ ይላል ሣሙኤል ዘሚካኤል። የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና መምህራን ያጨበጭቡለታል። ያሞቁለታል። እዚህ ላይ ሌላም ነገር ይጨምርላቸዋል። ከአውስትራሊያ ካምቢራ ዩኒቨርሲቲ በኮንስትራክሽን ማናጅመንት ቴክኖሎጂ የማስተርስ ድግሪውን ሲቀበል ከተማሪዎች ሁሉ የላቀ ውጤት አምጥቶ 500ሺ ዶላር የተሸለመ ኢትዮጵያዊ ሊቅ እንደሆነ በየ ዩኒቨርሲቲው ሲናገር ይጮህለታል። ከታላቁ የኘላኔታችን ዩኒቨርሲቲ የዶክተሬት ድግሪውን ሲሠራ ምርጥ ኢትዮጵያዊ ተብሎ መሸለሙን ለየዩኒቨርሲቲው ማሕበረሰብ ይናገራል። በቴሌቪዠን የሥራ ፈጠራ ዳኛ ሆኖ አስተያየት እየሰጠ ውጤት እየሰጠ ተወዳዳሪዎችን ሲጥልና ሲያሳልፍ ነበር። ሣሙኤል ዘሚካኤል የኢትዮጵያ ምሁር ላይ ምን ያልሆነው ነገር አለ? ግን አንዱም ተማሪ ወይም መምህር ጥያቄ አልጠየቀም።

ዛሬ በዚህ በሰለጠነው ዘመን መረጃ በየስልካችን ውስጥ ቁጭ ባለበት ዘመን ሣሙኤል ዘሚካኤል ተምሬበታለሁ የሚላቸውን ዩኒቨርሲቲዎች የጠየቀ ያጣራ ሰው አልነበረም። ተማረ አወቀ የምንለው ሕዝባችን እንኳን በቀላሉ እየተሸወደ ነው። ምስጋና ለአዲሰ ጣዕም የሬዲዮ ኘሮግራም ጋዜጠኞች ይሁንና የሣሙኤል ዘሚካኤልን ጉዶች አነፍንፈው ባይከታተሉና ባያጋልጡ ኖሮ ምናልባት ዘንድሮ ተወዳድሮ የፓርላማ አባል ሁሉ ይሆንብን ነበር። የእርሱ ፍላጐትም እንደዚያ ነበር። ያ ደግሞ ያለመከሰስ መብት ሁሉ ስለሚሰጠው ጉዳዩ ሌላ ታሪክ የይዝ ነበር።

ባጠቃላይ ሲታይ ባለማንበባችን ባለመመርመራችን የተለየ ነገር ይዘው የመጡ የሚመስሉን ሰዎች ሁለመናችንን ይሠርቁናል፤ ድህነት ሰፊ ነው ። አንዱ ድህነት አለማንበብ ነው። ማንበብ የዕውቀት ባለፀጋ ያደርገናል። ጠያቂ ያደርገናል። ስንጠይቅም መልስ ይኖራል። መልስ ውስጥ ደግሞ እውነትና ሀሰቱ ይገለፃል። 

ኢትዮጵያ ለዘመናት በተደራረበ ድህነት ውስጥ ያለች ሀገር ናት። አንዱ አመት ጥሩ ቢለበስ ቢበላ የሚቀጥለው አመት ላይ ችግር ጓዙን እየጠቀለለ የሚመጣባት ናት። ገበሬው እንኳን ሲናገር
ይኸ ቀን አለፈ ብላችሁ አትኩሩ
ድሕነት ቅርብ ነው ይመጣል ካገሩ
ይላል።


በጥጋብ ግዜ እንኳን የሚፈራባት አገር ነች። ምክንያቱም እንደ አዙሪት አልወጣ ያለ ችግር አለ። ድህነት አለ።
 በዚህ ድሃ ሕዝብ ውስጥ ብዙ ነገሮች ተአምር ይመስላሉ። የፍቼ ከተማውን ታምራት ገለታንም ማስወስ ይበቃል። ከተራ ዜጐች እስከ ታዋቂ አርቲስቶች በታምራት ገለታ የጥንቆላ ድርጊቶች ውስጥ ተመስጠው ገብተው ነበር። በኋላ ሁሉም ነገር አይሆኑ ሆነና ዘብርቅርቁ ወጣ።

ሀገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ ወንጌል ተሰብኳል ወይ? ብሎ የጠየቀኝ አንድ ጓደኛዬ ነበር። ምን ልበለው? የኢትዮጵያ ሕዝብ ስንት ሚሊየን ነው? ከዚያ ውስጥ ምን ያህሉ ወንጌልን ሲሰበክ ሰምቷል? ግን ግራ ገባኝና ሣልመልስለት ቀረሁ።

ዛሬ ካለችው ኢትዮጵያ ውስጥ ጳጳሳት ይሰደዱባታል። አንዲት ሀገር ጳጳስ ከተሰደደባት ምኑን የወንጌል ሀገር ሆነች? የጳጳሣት ስደት የአሜሪካንን የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ሃይማኖትን እያስፋፋ ነው። በውጭ ሀገር ሳይቀር ሌላ ሲኖዶስ መቋቋሙ ጸሀይ የሞቀው ሀገር ያወቀው ነገር ነው። ዲያቆናት እና ቀሣውስትም ስደታቸው በዝቷል። መዘምራን ከበሮ እና ጸናጽል እየያዙ በመውጣት በውጭ ሀገር ጥገኝነት እየጠየቁ ነው። ታዲያ ምኑን የወንጌል ሀገር ሆነች? ዲቪ ሎቶሪ የሚሞሉ የሀይማኖት አባቶች የበዙባት ሀገር ሆናለች።
በሀገር ውስጥም ቤተ-ክርስትያን አሠራሯ ለሙስና ተጋልጧል፤ ምዝበራ ዝርፊያ አለ እየተባለ በየጋዜጣው ሲወጣ እናነባለን። የጳጳሳት ፀብ እንሰማለን። አንዳንድ አፀያፊ የሆኑ ሃሜታዎችም አሉ። እነዚህ ነገሮች እየተደራረቡ እየበዙ ሲመጡ ወደየት እንደሚወስዱን አላውቅም። ሀገሪቱ አዲስ የእርቅና የሰላም ጥምቀት ሣያስፈልጋት አይቀርም።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቴሌቨዠን ኘሮግራሞች ላይ የሃይማኖት ዝግጅቶች እየቀረቡ ይገኛሉ። ኦርቶዶክስና ሌሎች የሃይማኖት ፍልስፍናዎችን የሚያራምዱ ቤተ እምነቶች  የአየር ሰዓት ወስደው እየሠሩ ነው። ግን ውዝግብና መካሠስም ሌላው የዘመኑ ገፅታ ሆኖ ብቅ ብሏል። በዚህ ንትርክ ውስጥ ዋናው ጉዳይ ፈጣሪ ይረሣል። ሀይማኖት ይረሣል። ጉዳዩ የሠዎች ፀብ ይሆናል። ስለዚህ ምዕምኑ ራሱ ግራ የገባው እየሆነ ነው። በዚህ ግራ በተጋባ ምዕምን ውስጥ ሌሎች ይገቡበትና ይዘውት ይነጉዳሉ።

በ1927 ዓ.ም የኢጣሊያ ፋሽስት ሰራዊት ኢትዮጵያን ሲወር ዝም ብሎ አልነበረም። ብዙ ኢትዮጵያዊያን ያውም የተማሩት ሁሉ ሣይቀሩ ባንዳ ሆነውለት ነው። ባንዳ የሆኑበት ምክንያት ሊለያይ ይችላል። ግን ለጠላት አድረዋል። የሃይማኖት አባቶች ሁሉ ሣይቀሩ ለኢጣሊያ ፋሽስቶች ሰብከዋል። ቀድሠዋል። ዘምረዋል። እንዲህ አይነት ሕዝብ እና የሀይማኖት ሰው እንዴት ተፈጠረ? ብለን መጠየቅ አለብን። ሐገረ ኢትዮጵያ እንዴት ተከዳች?

ይህ ጉዳይ ወደ ኋላ ተኪዶ መልስ የሚሠጥበት ሊሆን ይችላል። ቅድመ 1927 ዓም በተለይ አፄ ምኒልክ አረፉ ከተባለበት ጊዜ ጀምሮ ለሃያ አመታት የኢትዮጵያ ፖለቲካ ምን ነበር ብሎ ማሰብ ይጠይቃል። ሃይማኖቷስ እንዴት ነበር? ይህን ጥያቄ መወያያ ላድርገው። ምክንያቱም መልሱ ሰፊ ሊሆን ስለሚችል ነው። አድዋ ላይ 1888 ዓ.ም ጣሊያንን በአንድ ቀን ጦርነት ድል ያደረገ ሕዝብ ከ40 አመታት በኋላ የተፈጠሩት የእርሱ ልጆች ደግሞ ለኢጣሊያ ባንዳ ሲሆኑ ምክንያቱ ምንድን ነው? ለሚለው መልስ መስጠት ወደፊት ያስፈልጋል። ጉዳዩን እንደ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ክሽፈት ብዬ ብቻ የማልፈው ስላልሆነ ነው።
ሕዝባችን አቋም ያለው፤ በራሱ የሚተማመን፤ ለክሩ ለማተቡ ለእምነቱ የፀና፤ እንዲሆን ማንበብ መመርመር አለበት። ኢትዮጵያ 90 ሚሊዮን ሕዝብ እያላት ሦስት ሺ ኮፒ መፃሕፍት የምታሳትም አስገራሚ ምድር ነች። 90 ሚሊየን ሕዝብ እያላት 5 ሺ ኮፒ ጋዜጣ የምታሣትም ናት። ሕዝቡ ምን እያደረገ ነው ቀኑን የሚያሣልፈው? ብሎ የጠየቀኝ ኬኒያዊ ትዝ ይለኛል።

መጪው ጊዜ ፈጣን ነው። ሣይንስና ቴክኖሎጂው ላይ በላይ እየተጓዘ ነው። እኛ ገና ነን። ገና በተአምራቶች እየተነጋገርን እየተጨቃጨቅን የምንኖር ሆነናል። ማርሹን የግድ መቀየር አለብን። ከወዲያ በኩል ብርሃን አለ። አለም በስልጣኔ ብርሃን እየደማወቀ ነው። ወደ እሱ የሚያመራንን የንባብ የዕውቀት የመመርመር የመጠየቅ ባሕላችንን እንገንባው።

16 ሚሊየን ሕዝብ ተርቦብን የጥሬ ስጋ ኤግዚቢሽን ላይ አንራኮት። ሕዝባችንን እናስበው። እንርዳው። 16 ሚሊየን ሕዝብ ተርቦብን የማንቸስተር እና የአርሴናል ጨዋታ መንፈሣችንን አያሠቃየው። በዘመናችን እናስተውል፡፡

ምንጭ ፡- ሰንደቅ

5 comments:

  1. Enante yeseytan melktegna nachihu enihn abat kerbachihu satayu bekinat tenesastachihu asaserachiwachew yemtefelgut silehone enquan desalachihu gin yemigetmew andachim yemastemar siytet gin metkes atchilum yesachewun timhirt yeteketatele menfesawi gulbet endiagegn eredaw enji kebete kirstian endirk aladeregum egna gin yenanten maninet awukenal ande ante ande ato bituluachew minachewum aykenes legna enante sathonu aynachinina joroachin miskirachin new yenante ewuket chigir eyefeteru endih hone endih tefetere eyalu yemitsaf mefeleg kerbo meteyek ayto menager alfeterelachihum mikniatum benante yalmetaw hulu wenjelegna silehone gin e/her ale ewunet yashenfal

    ReplyDelete
    Replies
    1. ወንድሜ ለምን የሚመክርህን ወንድምህን ለመሳደብ ትፈጥናለህ? ለስድብም ፊት አትስጠው!!!!! አንተ ሰው የሚያይልህን አምላክ እስከመቼ ታመልካለህ? አንተ ማየት የቻልከውን ጌታ ብታመልክ እርግጠኛ ነኝ ይህንን የስድብ ቃላት አትጠቀመውም፡፡ ሙሉውን አንብበው፡፡ አንተ ከምትለው ጋር ጭራሽ አይገናኝም፡፡ የብዙዎቻችን ድካም እራሳችንን ትክክል አድርገን ማስቀመጣችን ነው፡፡ ግን አይደለም፤ መንፈስን ሁሉ መርምሩ ነው፡፡ የሚነገረንን ምክር ሁሉ ወደሌላ ለምን እንተረጉመዋለን፡፡ አንተ መምህር ግርማን ስለምትወዳቸውና ስለምታከብራቸው የሚነገረው ነገር ሁሉ እሷቸውን ለመቃረን የተፃፈ የሚመስልህ ከሆነ ተሳስተሀል፡፡ ወንድሜ ለአንተ ዋጋ የከፈለው ክርስቶስ ብቻ ነው፡፡ ሰው ሸንበቆ ነው ድጋፍ አይሆንም፤ እሳቸው እውነተኛ ከሆኑ እራሱ የእውነቱ ባለቤት ክርስቶስ ነፃ ያወጣቸዋል፡፡ ይህ የእኛ ስራ አይደለም፡፡ የእኛ ስራ ግን መሆን ያለበት እራሳችንን መፈለግና ከወደቅንበት ስፍራ ተነስተን ሕያው ሆኖ መገኘት ነው፡፡ ይህ ደግሞ የሚሆንም እውነቱን በመመርመር ነው፡፡ በማንበብ እራስን ፈልጎ ማግኘት ነው፡፡ እና ማስተዋሉን ይስጥህ ይስጠን፡፡

      Delete
  2. እውነት ነው ወንድሜ ቃለ-ሕይወት ያሰማልን፡፡ ጠዋት ያደናቀፈህ ድንጋይ ማታ ከደገመህ ድንጋዩ አንተ ነህ፡፡ ህዝባችን በተለያየ ጊዜ እንደዚህ ዓይነት ችግር ሲደርስብን መማር ነበረብን፡፡ ግን አሁንም ድረስ መማር አልቻለም፡፡ እግዚአብሔር ሀገራችንን ስለሚወዳት ነው በተለያየ መንገድ የሚያስተምረን፡፡ እኔ ስለራሴ ብናገር ደስ ይለኛል፡፡ እኔ የመምህር ግርማን ትምህርት እከታተላለሁኝ፡፡ ትምህርታቸውን እወደዋለሁኝ፡፡ ነገር ግን እንደዚህ ግን አሳድጄ አልከተላቸውም እንደማንኛውም መንፈሳዊት ትምህርት በድረገጽ ላይ ነው የምማረው፡፡ በተረፈ ግን ፈውሳቸውን ማጣራት ስለነበረብኝ አንድ ሁለት ቀን ብቻ ተገኝቼ ተመለከትኩት እኔ ብዙ የፈውሱ ኘሮግራም አልተመቸኝም፡፡ ብዙ ሰው ዳንኩኝ ይላል፡፡ እኔ ምንም ይሁን ሰው ሲደሰት ማየት ደስ ይላል፡፡ በቃ ከዚያ ያለፈ ነገር ግን የሚሰማኝ ነገር የለም፡፡ ብዙ ተጨንቄ ደግሞ በተአምር የማምን ሰው አይደለሁም፡፡ ምክንያቱም እኔ ብዙ የጤና ችግሮች ነበሩብኝ፡፡ እግዚአብሔር ይመስገን ማንንም ግን ተከትዬ አይደለም የተፈወስኩት ለእኔ ለራሴ ከተደረገልኝ በላይ ተዓምር የለም፡፡ የሚያውቁኝ ሁሉ እስከአሁን ድረስ እውነት አይመስላቸውም፡፡ ግን እግዚአብሔር ይመስገን ለመዳን ግን እንደሚሰማው ብዙ መንገላታት አልደረሰብኝም፡፡ በአቅራቢዬ በሚገኘው ቤተክርስቲያን በመገኘት ቤተክርስቲያኔ የምታዘውን ስርአተ ቤተክርስቲያን ብቻ በመፈጸም ነው የዳንኩት፡፡ አሁንም ቢሆን እኔ ሕክምና መሄድ ብዙ አልወድም ቤተክርስቲያኔ የምትለውን በመስማት ብቻ ነው የምፈወሰው፡፡ ፀበልም ለመጠቀም ስፈልግ የቤተክርስቲያን ስርአትን የሚጠብቅና ቢያንስ ቤተክርስቲያን ውስጥ መሆኑን ብቻ በማመን ነው ፀበሉን የምጠቀመው፡፡ እኔ አላውቅም እኔ ለመዳን እንደሚወራው 7 ቀን አይፈችብኝም በአንድ ቀን ነው የምድነው፡፡ ድንገትም ይህ ነገር የጠቀመኝ ቤተክርስቲያን ውስጥ ማደጌና የሰንበት ትምህርት ቤት መምህሬ ሳላመሰግነው አላልፍም በጣም ነው ከልብ የሚያስተምረው እኔም ከልቤ ነበር የምሰማው፡፡ እንደገናም ኮሌጅ ስማር ማህበረ ቅዱሳን ትምህርታቸውን እከታተል ነበርና የእነርሱም ትምህርት እረድቶኛል፡፡ እነርሱንም ሳለመሰግን አላልፍም፡፡ አሁን ደግሞ በኢንተርኔት የምመለከታቸውና የምከታተላቸው መንፈሳዊ ትምህርቶች ደግሞ እውነቱን እንደረዳ አድርገውኛል፡፡ ስለዚህ ሁሉም ሰው አብዛኛው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ የሆንን በተቻለን አቅም ቤተክርስቲያንን ዶግማ፣ቀኖና እና ስርአትን ጠንቅቆ መማርና ማወቅ እንደገናም በተግባር በማዋል የምንፈልገውን ጤና ብዙ ሳንገላታ የምናገኝ መሆኑን ጠንቅቀን አለማወቅ ይመስለኛል በተለያየ ተአምራት እየተጓዝን እየወደቅን ያለነው፡፡ ጤናችንም ለወራትና ለዓመታት እየፈጀ ጊዜያችንን የምንፈጀው ትልቁ ችግር የቤተክርስቲያንን አስተምሮን እንደልማድ እያየን እንጂ በትክክል በእውነትና በመንፈስ ሆነን ባለመቀበላችን መንፈሳዊነትን እንደአንድ መከራ መመልከታችን፣ ለዚህ ችግር በቀላሉ ለመውደቅ ተገደናል፡፡ ተኩላውም እንደዚሁ እየጣለን ይገኛል፡፡ ማስተዋሉን ይስጠን፡፡

    ReplyDelete
    Replies
    1. "በአቅራቢዬ በሚገኘው ቤተክርስቲያን በመገኘት ቤተክርስቲያኔ የምታዘውን ስርአተ ቤተክርስቲያን ብቻ በመፈጸም ነው የዳንኩት...."that is all ...lets hear from preachers who will teach us to follow our church not from those who will teach directly or indirectly to follow them

      Delete
  3. Bealubalta lay komo kemizebzeb ga indet and yihonal.Kealubalta tsidu.Iwunetin yazu.Atmaki Gima iwukina ayashachewum.Issu yawukachewal.meto aleka nebeu bilo mewashet min yitekmal. "Is" inji "Was" bekistna bota yelewum.Ahun pawulos asadaj newu?Geta wengelawiyanin kekesoch aydelem yewesedewu.Kewuchi inji.Inante teb keskashoch kentuwoch nachihu.bewendimamach mehakel tebini(hasetin) yeemiyamelalis issu igziabihe kehulum yemitelawu newu

    ReplyDelete